በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሐምሌ 11, 2019
ግሪክ

አቴንስ፣ ግሪክ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

አቴንስ፣ ግሪክ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከሐምሌ 5-7, 2019

  • ቦታ፦ በአቴንስ፣ ግሪክ የሚገኘው የአቴንስ ኦሎምፒክ ስታዲየም

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ሩሲያኛ፣ ሮማኒ (የደቡባዊ ግሪክ)፣ አልባኒያኛ፣ እንግሊዝኛ፣ የግሪክ ምልክት ቋንቋ፣ ግሪክኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 36,873

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 406

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 6,000

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ማዕከላዊ አውሮፓ፣ ሰሜን መቄዶንያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቱርክ፣ አልባኒያ፣ አርሜንያ፣ አውስትራሌዢያ፣ ኪርጊስታን፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን፣ ፊጂ

  • ተሞክሮ፦ አንድ የጉዞ ወኪል ሠራተኛ እንዲህ ብሏል፦ “በጉዞ ወኪል ውስጥ ረጅም ጊዜ ሠርቻለሁ፤ በየትኛውም አገር እንዲህ ያለ አደረጃጀት አይቼ አላውቅም። ትናንት ያየሁት ነገር በጣም አስገርሞኛል። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ 2,600 የሚያህሉ ተጓዦችን አደራጅታችኋል፤ ባለሙያዎቹ እንኳ እንዲህ ጥሩ አድርገው ማደራጀት አይችሉም። ይበልጥ ያስገረመኝ ግን ፈገግታችሁ ነው። ብዙ ዓመት ይህን ሥራ ስለሠራሁ ሰዎች ግዴታ ሆኖባቸው ፈገግ ሲሉና ከልባቸው ፈገግ ሲሉ መለየት እችላለሁ። የሁላችሁም ፈገግታ ልባዊ ነው።”

 

ስታዲየሙን ለስብሰባው ካዘጋጁት ከ4,000 የሚበልጡ ፈቃደኛ ሠራተኞች መካከል ጥቂቶቹ

ልጆች ወደ ግሪክ የመጡትን ልዑካን ሲቀበሉ

ከ406 ተጠማቂዎች መካከል አንዷ

በሮማኒ ቋንቋ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገኙ እህቶች ፎቶግራፍ ሲነሱ። ግሪክ ውስጥ በሮማኒ ቋንቋ ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው

ልዑካኑ በአካባቢው ከሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች ጋር ሲያገለግሉ

ልዑካኑ የግሪክ ቅርሶችን ሲጎበኙ

ምሽት ላይ በነበረው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ የቀረበው ድራማ ሐዋርያው ጳውሎስ በግሪክ ያከናወነውን አገልግሎት የሚያሳይ ነበር

ወንድሞችና እህቶች ሰርታኪ የተባለውን ባሕላዊ ውዝዋዜ ሲያሳዩ

አንዲህ እህት ቦውዞኪ የተባለውን የግሪክ ባሕላዊ የሙዚቃ መሣሪያ ስትጫወት

ልዑካኑ አንዳንድ ግሪክኛ ቃላትን ሲማሩ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ዴቪድ ስፕሌን የሦስተኛውን ቀን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ፤ ንግግሩ ወደ ግሪክኛ ተተርጉሟል

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በስብሰባው የመጨረሻ ቀን ላይ ሕዝቡን ሲሰናበቱ