ታሪካዊ እመርታዎች በደቡብ ኮሪያ
ጥቅምት 18, 2016—የግዋንግጁ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሦስት የይሖዋ ምሥክሮችን ይግባኝ ከሰማ በኋላ በሕሊናቸው ምክንያት የተከሰሱ ሰዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በነፃ ለቀቀ
ጥር 14, 2015—የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ፣ ደቡብ ኮሪያ የ50 የሕሊና ፍርደኞችን መብት እንደጣሰችና “አግባብነት ለሌለው እስር” እንደዳረገች ሪፖርት አደረገ
ጥቅምት 25, 2012—የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ፣ የይሖዋ ምሥክር ከሆኑ 388 የሕሊና ፍርደኞች ጋር በተያያዘ የሕሊና ነፃነታቸው እንደተጣሰ አሳወቀ
ነሐሴ 30, 2011—የአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት፣ በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት የማይሰጡ ሰዎችን የሚቀጣው ሕግ ሕገ መንግሥታዊ መሆኑን በድጋሚ አጸና
መጋቢት 24, 2011—የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ፣ የ100 የይሖዋ ምሥክሮች ሰነዶችን ከመረመረ በኋላ በሕሊና ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት አለመስጠት የግለሰቦች መብት እንደሆነ አረጋገጠ
መጋቢት 23, 2010—የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ፣ በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ 11 የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ሰዎች የሕሊና ነፃነታቸው እንደተጣሰ አሳወቀ
ጥር 15, 2009—ከ1975 እስከ 1985 ባሉት ዓመታት በእስር ላይ እያሉ ሕይወታቸው ላለፈ አምስት የይሖዋ ምሥክሮች ሞት መንግሥት ተጠያቂ እንደሆነ አንድ ፕሬዚዳንታዊ ሪፖርት አረጋገጠ
ኅዳር 3, 2006—የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ፣ ደቡብ ኮሪያ በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሁለት የይሖዋ ምሥክሮችን መብት እንደጣሰች አሳወቀ
ነሐሴ 26, 2004—የአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት፣ በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት የማይሰጡ ሰዎችን የሚቀጣው ሕግ ሕገ መንግሥታዊ መሆኑን አጸና
1975—መንግሥት፣ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ጀመረ
1973—መንግሥት፣ የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ማሠቃየት ጀመረ፤ ይህ ሁኔታ እስከ 1990ዎቹ አጋማሽ ቀጥሏል
1953—በሕሊና ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች መታሰር ጀመሩ
ጥቅምት 30, 1952—መንግሥት የይሖዋ ምሥክሮችን ሕጋዊ ማኅበር መዘገበ