በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ መስከረም 26, 2024፣ ኸሊን የተባለችው አውሎ ነፋስ በሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ ላይ። በስተ ቀኝ ከላይ፦ በጎርፍ የተጥለቀለቀ የስብሰባ አዳራሽ በስዋናኖኣ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ዩ.ኤስ.ሴ። በስተ ቀኝ ከታች፦ በአሽቪል፣ ኖርዝ ካሮላይና የአንድ ወንድም ቤት አውሎ ነፋስ የጣላቸው ግንዶች ተከምረውበት

ጥቅምት 3, 2024
ዩናይትድ ስቴትስ

ኸሊን የተባለችው አውሎ ነፋስ ደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስን መታች

ኸሊን የተባለችው አውሎ ነፋስ ደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስን መታች

መስከረም 26, 2024 የፍሎሪዳ፣ ዩ ኤስ ኤ ባሕረ ሰላጤ ኸሊን በተባለችውና እርከን 4 ደረጃ በተሰጣት ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተመትቷል። ይህች አውዳሚ አውሎ ነፋስ ከባድ ዝናብ የቀላቀለች ስትሆን በሰዓት እስከ 225 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ፍጥነት ስትጓዝ ነበር። መስከረም 27 ደግሞ በጆርጂያ በሰዓት 95 ኪሎ ሜትር የሚጓዝና ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ ነፋስ አስነስታለች። በቀጣዩ ቀን ኸሊን ወደ ሰሜን በማቅናት ሳውዝ ካሮላይናን የመታች ሲሆን ቢያንስ ሦስት አውሎ ነፋሶችን አስነስታለች። በኋላም ኖርዝ ካሮላይና ስትደርስ በበርካታ ከተሞች ላይ ከ90 ሴንቲ ሜትር በላይ መጠን ያለው ዝናብ ጥሏል።

አውሎ ነፋሷ ያመጣችው ዝናብ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ያስከተለ ሲሆን በቤቶች፣ በንግድ ቦታዎችና በመንገዶች ላይ ጉዳት አድርሷል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችም ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸዋል። ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ቢያንስ 180 ይሆናል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 3 ወንድሞች ሕይወታቸውን ማጣታቸው አሳዝኖናል

  • 7 አስፋፊዎች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1,606 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 29 ቤቶች ወድመዋል

  • 236 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 779 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

  • 19 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ ሽማግሌዎች በአውሎ ነፋሱ ለተጎዱት መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው

  • የእርዳታ ሥራውን የሚያስተባብሩ 2 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

በዚህች ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ምክንያት ሕይወት በመጥፋቱ አዝነናል። ይሖዋ መላውን የሰው ዘር በተመለከተ “ተረጋግቶ ይኖራል፤ መከራ ይደርስብኛል የሚል ስጋትም አያድርበትም” በማለት በሰጠው ተስፋ እንጽናናለን።—ምሳሌ 1:33