በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ዓለም አቀፋዊ ዜና

በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮች—በአገር

በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮች—በአገር

በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮች እስከ ኅዳር 2024

ቦታ

የታሰሩት ብዛት

የታሰሩበት ምክንያት

ሩሲያ

131

  • ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ

ሲንጋፖር

8

  • ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን

ኤርትራ

64

  • ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ

  • ምክንያቱ አልተገለጸም

ክራይሚያ

12

  • ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ

ሌሎች አገራት

ከ10 በላይ

  • ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ

ድምር

ከ225 በላይ

 

የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ 18 እንደሚገልጸው “የሐሳብ፣ የሕሊና እና የሃይማኖት ነፃነት” መሠረታዊ የሆነ ሰብዓዊ መብት ነው። a ይሁንና በአንዳንድ አገራት የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ይህን መሠረታዊ መብት የተነፈጉ ሲሆን ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ታስረዋል፤ ይባስ ብሎም አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች የጭካኔ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል። አብዛኞቹ የይሖዋ ምሥክሮች የታሰሩት አምልኳቸውን በማካሄዳቸው ምክንያት ብቻ ነው። ሌሎቹ ደግሞ የታሰሩት በሕሊናቸው ምክንያት ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው።

a በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 18⁠ን እና የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 9⁠ን ተመልከት።