በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኅዳር 14, 2024
ኪርጊስታን

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በኪርጊዝ ቋንቋ ወጣ

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በኪርጊዝ ቋንቋ ወጣ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጄፍሪ ዊንደር የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በኪርጊዝ ቋንቋ መውጣቱን ኅዳር 9, 2024 አብስሯል። ይህ ምሥራች የተነገረው በኪርጊስታን ቅርንጫፍ ቢሮ በተዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም ላይ ነበር። በፕሮግራሙ ላይ 147 ታዳሚዎች በአካል የተገኙ ሲሆን ሌሎች 3,044 ሰዎች ደግሞ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ፕሮግራሙን ተከታትለዋል። ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም የወንጌሎችና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የድምፅ ቅጂዎችም ወዲያውኑ በ​jw.org እና JW Library አፕሊኬሽን ላይ ተለቅቀዋል። የታተመው ቅጂ በ2025 ይወጣል።

የይሖዋ ምሥክሮች በኪርጊዝ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን መተርጎም ከጀመሩ 30 ዓመታት ገደማ ሆኗቸዋል። በአሁኑ ወቅት በ43 ጉባኤዎችና ቡድኖች ውስጥ የሚያገለግሉትን ከ2,800 በላይ ወንድሞችና እህቶችን ጨምሮ 5 ሚሊዮን ገደማ የኪርጊዝ ቋንቋ ተናጋሪዎች በመላዋ ኪርጊስታን ይኖራሉ።