ነሐሴ 8, 2019
ኔዘርላንድስ
ዩትሬክት፣ ኔዘርላንድስ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከነሐሴ 2-4, 2019
ቦታ፦ በዩትሬክት፣ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ያርበርስ ሃለንኮምፕሌክስ
ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ ችዊ፣ አረብኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ደች፣ ደች ምልክት ቋንቋ፣ ፓፒያሜንቶ፣ ፖሊሽ፣ ፖርቱጋልኛ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 42,335
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 212
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 6,000
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሩማኒያ፣ ሱሪናም፣ ቤልጅየም፣ ብራዚል፣ አውስትራሌዢያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ፖርቱጋል
ተሞክሮ፦ ያርበርስ ሃለንኮምፕሌክስ ቦታውን የሚያጸዳ ድርጅት ቀጥሮ ነበር። በዚህ የጽዳት ድርጅት ውስጥ የሚሠራ አንድ ወንድም ነበር፤ የድርጅቱ ኃላፊ ለዚህ ወንድም ስልክ ደውሎ እንዲህ አለው፦ “እዚህ ያሉት ሰዎች የተስማማነውን ነገር በሙሉ ጊዜውን ጠብቀው ይሠራሉ፤ ባወጡት ፕሮግራም መሠረት ሕንፃውንና አካባቢውን በሙሉ ሙልጭ አድርገው አጽድተዋል። ሕንፃውን ስናስረክባቸው ከነበረው ይበልጥ ጽዱ አድርገው የሚመልሱልን ይመስለኛል። በጣም የሚገርም ነው! እንዲህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ የማይውሉትን የምግብ ቤቱን ክፍሎች ጭምር አጽድተዋል! በማንኛውም ሰዓት ወደ መጸዳጃ ቤቶቹ ብትሄድ ጽዳቱን የሚከታተሉ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፤ የትኛውም ቦታ ችግር ቢያጋጥም ወዲያውኑ መጥተው ችግሩን የሚፈቱ ሰዎች አሉ! እንዲህ ያለ ነገር ጨርሶ አጋጥሞኝ አያውቅም።”
የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ልዑካኑን አውሮፕላን ማረፊያ ሄደው ሲቀበሉ
ቤቴላውያን የኔዘርላንድስን ቅርንጫፍ ቢሮ ለመጎብኘት የመጡ ልዑካንን ሰላም ሲሉ
አንዲት ልዑክ ከአካባቢው እህት ጋር ሆና ሰዎችን ለስብሰባው ስትጋብዝ
ወንድሞችና እህቶች በያርበርስ ሃለንኮምፕሌክስ ዋነኛ አዳራሽ ሆነው ስብሰባውን ሲከታተሉ። ስብሰባው በሌሎች አምስት አዳራሾችም ተላልፏል
በስብሰባው ላይ ከተጠመቁት 212 ወንድሞችና እህቶች መካከል አንዳንዶቹ
ወንድሞችና እህቶች በስብሰባው ወቅት ማስታወሻ እየያዙ በትኩረት ሲከታተሉ
ከተለያዩ አገራት የመጡ ልዑካን ስጦታ ሲለዋወጡ
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጄፍሪ ጃክሰን የእሁዱን ስብሰባ የመጨረሻ ንግግር ሲያቀርብ
ሚስዮናውያንና ሌሎች የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በስብሰባው መደምደሚያ ላይ ተሰብሳቢዎቹን ሲሰናበቱ