የካቲት 13, 2024
ሩሲያ
ይሖዋን ማገልገል በሚያስገኘው ክብር ላይ አተኩረዋል
በክራስኖዳር ግዛት የሚገኘው የቭይሴልኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዬቭጌኒ ቦችኮ፣ ቭላድሚር ኮሌስኒኮቭ፣ አሌክሴ ሹብኒኮቭ፣ ቪታሊ ኡሻኮቭ እና ቫለሪ ቬችካዬቭ ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ለእነዚህ ወንድሞችም ሆነ የእሱን ድጋፍ ለሚሹት ሁሉ ደስታና ብርታት መስጠቱን እንደሚቀጥል አንጠራጠርም።—መዝሙር 141:8
የክሱ ሂደት
የካቲት 11, 2022
ዬቭጌኒ፣ አሌክሴ፣ ቪታሊ እና ቫለሪ የክስ ፋይል ተከፈተባቸው
የካቲት 13, 2022
ቤቶቻቸው ተፈተሹ። ዬቭጌኒ፣ አሌክሴ እና ቪታሊ ምርመራ ተደረገባቸው። ቪታሊ ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ
የካቲት 15, 2022
ቪታሊ ማረፊያ ቤት ገባ
የካቲት 16, 2022
ዬቭጌኒ እና አሌክሴ የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው
የካቲት 18, 2022
ቫለሪ የጉዞ ገደብ ተጣለበት
የካቲት 21, 2022
ቭላድሚር የክስ ፋይል ተከፈተበት
መጋቢት 15, 2022
ቭላድሚር የጉዞ ገደብ ተጣለበት። ክሳቸው በአንድ መዝገብ ተጠቃለለ
መስከረም 8, 2022
ቪታሊ ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ ከዚያም የቁም እስረኛ ተደረገ
ጥቅምት 10, 2022
ቪታሊ ከቁም እስር ተፈታ፤ ከዚያም የጉዞ ገደብ ተጣለበት
ግንቦት 31, 2023
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ