በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሜክሲኮ የሚገኙት አዳዲሶቹ የርቀት ትርጉም ቢሮዎችና መኖሪያዎች ሥራ ጀምረዋል። በስተግራ፦ ሶትሲል፣ በስተቀኝ ከላይ፦ ዛፖቴክ (ኢስመስ) እና በስተቀኝ ከታች፦ ኦቶሚ (ሜስኪታል ቫሊ)

ነሐሴ 31, 2022
ሜክሲኮ

በማዕከላዊ አሜሪካ የርቀት ትርጉም ቢሮዎች ቁጥር 25 ደረሰ

በማዕከላዊ አሜሪካ የርቀት ትርጉም ቢሮዎች ቁጥር 25 ደረሰ

ከጥር እስከ ሐምሌ 2022 ባለው ጊዜ ሜክሲኮ ውስጥ አምስት አዳዲስ የርቀት ትርጉም ቢሮዎች ሥራ ጀምረዋል። በመሆኑም በማዕከላዊ አሜሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ ክልል ሥር የሚገኙት የርቀት ትርጉም ቢሮዎች ቁጥር 25 ደርሷል። አዳዲሶቹ የርቀት ትርጉም ቢሮዎች የታራስካን፣ የሶትሲል፣ የዛፖቴክ (ኢስመስ)፣ የኦቶሚ (ሜስኪታል ቫሊ) እና የቾል የትርጉም ቡድኖች፣ ቋንቋዎቹ በብዛት በሚነገሩባቸው አካባቢዎች እንዲኖሩ ያስችላሉ። በቀጣዩቹ ወራት በማዕከላዊ አሜርካ ቅርንጫፍ ቢሮ ክልል ሥር 8 ተጨማሪ የርቀት ትርጉም ቢሮዎች ይከፈታሉ፤ እንዲሁም 34 ተጨማሪ የትርጉም ቢሮ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እቅድ ተይዟል።

ተርጓሚዎች ቋንቋው በስፋት በሚነገርበት አካባቢ መኖራቸውና መሥራታቸው ብዙ ጥቅሞች አሉት። ቀደም ሲል በቅርጫፍ ቢሮው ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ያገለገልችው የሶትሲል ትርጉም ቡድን አባል የሆነችው እህት ማርሴላ ኸርናንዴዝ እንዲህ ብላለች፦ “ቅርንጫፍ ቢሮው ውስጥ አገለግል በነበረበት ወቅት የምጠቅመባቸው ዓረፍተ ነገሮች በጣም የተወሳሰቡ እንደሆኑ አስተውያለሁ። አሁን ግን በቋንቋው በሚመራ ጉባኤ ውስጥ ያሉ ወንድሞችና እህቶች እርስ በርስ ሲያወሩም ሆነ ሲሰብኩ መስማቴ የቋንቋውን ለዛ በጠበቀ መልኩ እንድተርጉም አስችሎኛል።”

የእነዚህ የርቀት ትርጉም ቢሮዎች ንጽሕናና ውበት የአካባቢውን ሰዎች ትኩረት ስቧል። ሰዎች እነዚህን ሕንፃዎች ቆመው ሲያደንቁ አልፎ ተርፎም ፎቶ ሲያነሱ ማየት የተለመደ ነው። ከአንዱ የርቀት ትርጉም ቢሮ ፊትለፊት አነስተኛ ሱቅ ያላት አንዲት ሴት በትርጉም ቢሮው ውስጥ ምን እንደሚከናወን ካወቀች በኋላ በሯ ላይ ያለውን የእግረኛ መተላለፊያ አዘውትራ መጥረግና ሱቋን ማጽዳት ጀመረች። ይህን የምታደርግበትን ምክንያት ስትገልጽ “ከፊትለፊቴ ያለው እኮ ለአምላክ አገልግሎት የሚቀርብበት ሕንፃ ነው” በማለት ተናግራለች።

የእነዚህን የርቀት ትርጉም ቢሮውች ፕሮጀክት ይሖዋ እንደባረከው ግልጽ ነው። ከትርጉም ሥራዎች ጋር በተያያዘ ለምናገኛቸው ስኬቶች ሁሉ ምስጋና የሚገባው እሱ ነው።—መዝሙር 127:1