በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለታዳጊ ወጣቶች

ሙሴ ልዩ ኃላፊነት ተሰጠው

ሙሴ ልዩ ኃላፊነት ተሰጠው

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው ሆነህ የሚከናወነውን ነገር እንደምትከታተል አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ይሖዋ አምላክና ሙሴ

ታሪኩ በአጭሩ፦ ሙሴ እስራኤላውያንን እየመራ ከግብፅ እንዲያወጣቸው ይሖዋ አዘዘው።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፀአት 3:1-14⁠ን እና 4:1-17ን አንብብ።

የሚነደው ቁጥቋጦ ምን ሊመስል እንደሚችል ግለጽ።

․․․․․

በ⁠ዘፀአት 3:4 ላይ እንደሚገኘው አምላክ ሙሴን ሲያናግረውና ሙሴ ምላሽ ሲሰጥ ፊቱ ላይ ምን ዓይነት ስሜት ይነበብ የነበረ ይመስልሃል? የድምፁ ቃናስ ምን ዓይነት ሊሆን ይችላል?

․․․․․

ሙሴ በ⁠ዘፀአት 3:11, 13 እና 4:1, 10 ላይ ተመዝግበው የሚገኙትን ጥያቄዎች ለይሖዋ ሲያቀርብ ምን ዓይነት ስሜት የነበረው ይመስልሃል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ” የሚለው ሐረግ ምን ትርጉም እንዳለው ለማወቅ ሞክር። (ዘፀአት 3:14 NW) ሙሴ ስለ ይሖዋ ስም ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ይሖዋ እንዲህ ያለ መልስ የሰጠው ለምን ይመስልሃል? *

․․․․․

ሙሴ በፈርዖን ፊት ለመቅረብ ያመነታው ለምን ይመስልሃል? (ፍንጭ፦ ዘኍልቍ 12:3⁠ን አንብብ።)

․․․․․

ሙሴ፣ ወገኖቹ በሆኑት እስራኤላውያን ፊት ለመቅረብ ያመነታውስ ለምን ሊሆን ይችላል?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ሰዎች በራስ የመተማመን ስሜት ስለሚያጡበት ምክንያት

․․․․․

ይሖዋ በአንተና ባሉህ ችሎታዎች ላይ ስላለው እምነት

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር፦

በራስ የመተማመን ስሜት የምታጣው በየትኞቹ የሕይወትህ ዘርፎች ነው?

․․․․․

የአቅም ገደብ ቢኖርብህም እንኳ ይሖዋ በየትኞቹ መንገዶች ሊጠቀምብህ ይችላል?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

ይህን ዓምድ www.isa4310.com በተባለው ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.14 የይሖዋ ምሥክሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ወቅት ጥልቀት ያለው ምርምር እንድታደርግ ሊረዱህ የሚችሉ በርካታ መጻሕፍትንና ብሮሹሮችን አዘጋጅተዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በአካባቢህ ያሉትን የይሖዋ ምሥክሮች መጠየቅ ወይም ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች መጻፍ ትችላለህ።