ኢየሱስ አድማጮቹን አስደነቀ
ለወጣት አንባቢያን
ኢየሱስ አድማጮቹን አስደነቀ
መመሪያ:- ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳልና በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማት ሞክር። እንዲሁም የባለ ታሪኮቹን ስሜት ለመረዳትና ታሪኮቹ ሕያው እንዲሆኑልህ ጥረት አድርግ።
ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ሉቃስ 2:41-47ን አንብብ።
በቁጥር 46 ላይ የተጠቀሱት መምህራን ከኢየሱስ ጋር ስለ ምን ጉዳይ የተወያዩ ይመስልሃል?
․․․․․
ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ኢየሱስ ገና ትንሽ ልጅ ቢሆንም እንኳ ከሃይማኖት ምሁራኑ ጋር መወያየት የቻለው ለምን ይመስልሃል? ፍጹም ስለነበር ነው ወይስ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት አለ?
․․․․․
ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ሉቃስ 2:48-52ን አንብብ።
ኢየሱስ “ለምን ፈለጋችሁኝ?” ብሎ የጠየቃቸው በምን ዓይነት ስሜት ይመስልሃል?
․․․․․
ኢየሱስ ለወላጆቹ በቁጣ ወይም አክብሮት በጎደለው መንገድ እንዳልመለሰላቸው እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?
․․․․․
ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ዮሴፍና ማርያም መጨነቃቸው ተገቢ ነበር የምንለው ለምንድን ነው?
․․․․․
ኢየሱስ ፍጹም ቢሆንም እንኳ ለወላጆቹ መታዘዝ የነበረበት ለምንድን ነው?
․․․․․
ኢየሱስ ሲያደንቁት በነበሩት ሰዎች ፊት ወላጆቹ ሲቆጡት ቅር ያለው ይመስልሃል?
․․․․․
ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ።
ስለ መታዘዝ።
․․․․․
አንድ ሰው፣ ልጅ ሳለ የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት ማግኘቱ ስላለው ጠቀሜታ።
․․․․․
ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው የትኛው ሁኔታ ነው? ለምንስ?
․․․․․