ይሖዋ ፍቅሩን ያሳየን በየትኞቹ መንገዶች ነው?
“አብ ምን ያህል ታላቅ ፍቅር እንዳሳየን ተመልከቱ!”—1 ዮሐ. 3:1
መዝሙሮች፦ 91, 13
1. ሐዋርያው ዮሐንስ ክርስቲያኖች ስለ ምን ጉዳይ እንዲያስቡ አበረታቷል? ለምንስ?
ሐዋርያው ዮሐንስ በ1 ዮሐንስ 3:1 ላይ ያሰፈረውን ሐሳብ በጥልቀትና በአድናቆት ልናስብበት ይገባል። ዮሐንስ “አብ ምን ያህል ታላቅ ፍቅር እንዳሳየን ተመልከቱ” ሲል ክርስቲያኖች አምላክ ለእነሱ ያለው ፍቅር ምን ያህል ጥልቅና ሰፊ እንደሆነ እንዲሁም ፍቅሩን ያሳየበትን መንገድ እንዲያስቡ ማበረታታቱ ነበር። ከዚህ አንጻር የይሖዋን ፍቅር መረዳት ከቻልን ለእሱ ያለን ፍቅር ያድጋል፤ እንዲሁም ከእሱ ጋር ያለን ዝምድና ይጠናከራል።
2. አንዳንዶች አምላክ እንደሚወዳቸው መቀበል የሚከብዳቸው ለምንድን ነው?
2 ይሁንና አንዳንዶች አምላክ ሰዎችን ይወዳል የሚለው ሐሳብ አይዋጥላቸውም። አምላክ፣ ሰዎች እንዲፈሩትና እንዲታዘዙት ብቻ የሚፈልግ አካል እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። አሊያም በውስጣቸው ሥር ከሰደደ የተሳሳተ ትምህርት የተነሳ ሊሆን ይችላል አምላክ አፍቃሪ እንዳልሆነና እነሱም ሊወዱት እንደማይችሉ ይሰማቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ የፈለጉትን ነገር ቢያደርጉም ወይም የሚጠበቅባቸውን ነገር ሳያደርጉ ቢቀሩም እንኳ አምላክ እንደሚወዳቸው የሚያምኑ ሰዎች አሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠና ፍቅር የይሖዋ ዋነኛ ባሕርይ እንደሆነና ለእኛ ሲል ልጁን ቤዛ አድርጎ እንዲሰጥ ያነሳሳውም ፍቅር መሆኑን ተምረሃል። (ዮሐ. 3:16፤ 1 ዮሐ. 4:8) ይሁንና አስተዳደግህ ወይም ያሳለፍከው ሕይወት አምላክ ለአንተ ስላለው ፍቅር ባለህ አመለካከት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
3. አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር እንድንገነዘብ የሚረዳን የትኛው መሠረታዊ እውነት ነው?
3 ታዲያ ይሖዋ ለእኛ ያለውን ፍቅር ያሳየው በየትኞቹ መንገዶች ነው? መዝሙር 100:3-5ን አንብብ።) ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ አዳምን “የአምላክ ልጅ” ብሎ ይጠራዋል፤ ኢየሱስ ደግሞ ተከታዮቹን ወደ አምላክ ሲጸልዩ “በሰማያት የምትኖር አባታችን” ብለው እንዲጠሩት አስተምሯቸዋል። (ሉቃስ 3:38፤ ማቴ. 6:9) ይሖዋ ሕይወት ሰጪ ስለሆነ አባታችን ነው፤ በእኛና በእሱ መካከል ያለው ዝምድና በአንድ አባትና በልጆቹ መካከል ካለው ዝምድና ጋር ሊመሳሰል ይችላል። በአጭር አነጋገር አንድ ጥሩ አባት ልጆቹን እንደሚወድ ሁሉ ይሖዋም እኛን ይወደናል።
የዚህ ጥያቄ መልስ የተመካው በይሖዋ አምላክና በእኛ መካከል ያለውን ዝምድና በመገንዘባችን ላይ ነው። ይሖዋ የሰው ልጆች ሁሉ ፈጣሪ ነው። (4. (ሀ) ይሖዋ ከሰብዓዊ አባቶች የሚለየው እንዴት ነው? (ለ) በዚህና በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ምን እንመለከታለን?
4 እርግጥ ሰብዓዊ አባቶች ፍጹም አይደሉም። የፈለጉትን ያህል ጥረት ቢያደርጉም እንኳ ይሖዋ አባታዊ ፍቅሩን ያሳየበትን መንገድ ሙሉ በሙሉ ማንጸባረቅ አይችሉም። እንዲያውም አንዳንዶች ልጅ ሳሉ በቤተሰባቸው ውስጥ ካጋጠማቸው ሁኔታ የተነሳ በስሜታቸው ወይም በአእምሯቸው ላይ የማይሽር ጠባሳ የተወ መጥፎ ትዝታ አላቸው። ይህ ስሜታቸውን ጎድቶትና አሳዛኝ ሁኔታ አስከትሎባቸው ሊሆን ይችላል። ይሖዋ እንዲህ ዓይነት አባት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን እንችላለን። (መዝ. 27:10) ይሖዋ ምን ያህል እንደሚወደንና እንዴት እንደሚንከባከበን ማወቃችን ወደ እሱ እንድንቀርብ እንደሚያደርገን የታወቀ ነው። (ያዕ. 4:8) በዚህ ጥናት ላይ ይሖዋ እኛን እንደሚወደን ያሳየባቸውን አራት መንገዶች እንመለከታለን። በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ደግሞ እኛ ለእሱ ያለንን ፍቅር መግለጽ የምንችልባቸውን አራት መንገዶች እናያለን።
ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ የሚያስፈልገንን ይሰጠናል
5. ሐዋርያው ጳውሎስ ለአቴንስ ነዋሪዎች ስለ አምላክ ምን ነገራቸው?
5 ሐዋርያው ጳውሎስ በአቴንስ፣ ግሪክ እያለ ሰዎች ሕይወትንና ለሕይወት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ይሰጣሉ ብለው በሚያምኑባቸው አማልክት ከተማዋ መሞላቷን አስተዋለ። ከዚህም የተነሳ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ለመናገር ተገፋፍቷል፦ “ዓለምንና በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረው አምላክ . . . ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው እሱ ስለሆነ . . . ሕይወት ያገኘነው፣ የምንንቀሳቀሰውና የምንኖረው በእሱ ነው።” (ሥራ 17:24, 25, 28) አዎ፣ ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ በሕይወት ለመኖር የሚያስፈልገንን “ማንኛውንም ነገር” ይሰጠናል። እስቲ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ለማሰብ ሞክር።
6. የምድር አፈጣጠር አምላክ እንደሚወደን የሚያሳየው እንዴት ነው? (በመግቢያው ላይ ያለውን ፎቶግራፍ ተመልከት።)
6 ሁሉን ነገር የፈጠረው ይሖዋ ‘ለሰው ልጆች የሰጣትን’ ምድርን እንደ ምሳሌ እንመልከት። (መዝ. 115:15, 16) የሳይንስ ሊቃውንት ምድርን የሚመስሉ ሌሎች ፕላኔቶችን ለማግኘት በሕዋ ላይ ለሚያደርጉት ምርምር ይህ ነው የማይባል መዋዕለ ነዋይ አፍስሰዋል። እነዚህ ሊቃውንት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፕላኔቶችን ያገኙ ቢሆንም አንዳቸውም እንደ ምድር ለሰው መኖሪያነት ምቹ ሁኔታ ያላቸው ባለመሆናቸው በውጤቱ አልተደሰቱም። አምላክ ከፈጠራቸው ነገሮች ሁሉ ምድር በዓይነቷ ልዩ ነች። እስቲ አስበው፣ በፍኖተ ሐሊብና ከዚያ ውጭ ከሚገኙት ቁጥራቸው በውል ከማይታወቅ ፕላኔቶች መካከል ይሖዋ ምድርን መኖሪያ እንድትሆን ብቻ ሳይሆን ለፈጠራቸው ሰዎች ምቹ፣ ውብና ተስማሚ መኖሪያ አድርጎ አዘጋጅቷታል! (ኢሳ. 45:18) ይህም ይሖዋ ምን ያህል እንደሚወደን ያሳያል።—ኢዮብ 38:4, 7ን እና መዝሙር 8:3-5ን አንብብ።
7. አምላክ እኛን የፈጠረበት መንገድ በእርግጥ እንደሚወደን የሚያሳየው እንዴት ነው?
7 ይሖዋ ግሩም የሆነ መኖሪያ የፈጠረልን ቢሆንም እንኳ ደስታና እርካታ አግኝተን እንድንኖር ከቁሳዊ ነገር ይበልጥ የሚያስፈልገን ሌላ ነገር እንዳለ ያውቃል። አንድ ልጅ ወላጆቹ እንደሚወዱትና እንደሚንከባከቡት ሲያውቅ ይረጋጋል። ይሖዋ ሰዎችን በራሱ መልክ ሲፈጥር በውስጣቸው መንፈሳዊ ዘፍ. 1:27) ኢየሱስም “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው” ብሏል። (ማቴ. 5:3) ይሖዋ እንደ አንድ አፍቃሪ አባት በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ “የሚያስደስቱንን ነገሮች ሁሉ አትረፍርፎ [ይሰጠናል]።”—1 ጢሞ. 6:17፤ መዝ. 145:16
ፍላጎት ቀርጾባቸዋል፤ ይህም የሚያሳያቸውን ፍቅርም ሆነ የሚያደርግላቸውን እንክብካቤ መገንዘብና ምላሽ መስጠት ያስችላቸዋል። (ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ እውነትን ያስተምረናል
8. “የእውነት አምላክ” ወደሆነው ወደ ይሖዋ ዞር ማለት ያለብን ለምንድን ነው?
8 ሰብዓዊ አባቶች ልጆቻቸውን ስለሚወዱ ልጆቻቸው እንዳይሳሳቱ ወይም እንዳይታለሉ ጥበቃ ያደርጉላቸዋል። ይሁን እንጂ በርካታ ወላጆች እነሱ ራሳቸው በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙትን መሥፈርቶች ስለማይቀበሉ ለልጆቻቸው ተገቢ መመሪያ መስጠት አይችሉም። ይህም አብዛኛውን ጊዜ ግራ መጋባትና ብስጭት ያስከትላል። (ምሳሌ 14:12) በአንጻሩ ግን ይሖዋ “የእውነት አምላክ” ስለሆነ ለልጆቹ ከሁሉ የተሻለውን መመሪያ ይሰጣል። (መዝ. 31:5) ይሖዋ ልጆቹን የሚወዳቸው ከመሆኑም ሌላ በማንኛውም የሕይወታቸው ዘርፍ በተለይ ደግሞ ከአምልኮ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች መመሪያ እንዲሆናቸው የእውነትን ብርሃን ያበራላቸዋል። (መዝሙር 43:3ን አንብብ።) ይሖዋ የገለጠልን እውነት ምንድን ነው? ይህስ እሱ እንደሚወደን የሚያሳየው እንዴት ነው?
9, 10. ይሖዋ (ሀ) ስለ ራሱ ማንነት (ለ) ስለ እኛ ማንነት እውነቱን መግለጡ ፍቅሩን የሚያሳየው እንዴት ነው?
9 በመጀመሪያ ደረጃ ይሖዋ የራሱን ማንነት በተመለከተ እውነቱን ገልጦልናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሌሎች ስሞች ሁሉ ይበልጥ በብዛት ተጠቅሶ የሚገኘውን የግል ስሙን አሳውቆናል። ይሖዋ በዚህ መንገድ እሱን እንድናውቀው በማድረግ ወደ እኛ ይቀርባል። (ያዕ. 4:8) በተጨማሪም ይሖዋ ባሕርያቱን በመግለጥ ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ አሳውቆናል። ግዑዙ ጽንፈ ዓለም ኃይሉንና ጥበቡን የሚያሳይ ቢሆንም ይሖዋ በቅዱሳን መጻሕፍት አማካኝነት ፍትሑን በተለይ ደግሞ ገደብ የሌለውን ፍቅሩን ገልጦልናል። (ሮም 1:20) ይሖዋ፣ ኃይልና ጥበብ ብቻ ሳይሆን ፍትሕና ፍቅር ያለው አባት ስለሆነ ልጆቹ ወደ እሱ መቅረብ አይከብዳቸውም።
10 ይሖዋ ለእኛ ጥቅም ሲል ስለ እኛ ማንነት እውነቱን የገለጠልን ሲሆን በእሱ ዝግጅት ውስጥ ያለንን ቦታ አሳውቆናል። ይህም በጽንፈ ዓለማዊ ቤተሰቡ ውስጥ ሰላምና ሥርዓት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያበረክታል። ሰዎች ያለ አምላክ እርዳታ ራሳቸውን በራሳቸው መምራት እንደማይችሉ እንዲሁም ይህን መሠረታዊ እውነት ችላ ማለት አሳዛኝ መዘዝ እንደሚያስከትል ከመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ችለናል። (ኤር. 10:23) ይህ ለደህንነታችን ወሳኝ ነገር ነው። ሰላምና አንድነት ሊኖረን የሚችለው ለአምላክ ሥልጣን እውቅና የምንሰጥ ከሆነ ብቻ ነው። ይሖዋ ይህን አስፈላጊ እውነት ለእኛ መግለጡ ታላቅ ፍቅሩን የሚያሳይ አይደለም?
11. ይሖዋ እንደሚወደንና እንደሚያስብልን የሚያሳይ ምን ተስፋ ሰጥቶናል?
11 አንድ አፍቃሪ አባት ልጆቹ ትርጉምና ዓላማ ያለው ሕይወት እንዲመሩ ስለሚፈልግ የእነሱ የወደፊት ሕይወት በጥልቅ ያሳስበዋል። የሚያሳዝነው ግን አብዛኞቹ ሰዎች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ አመለካከት የላቸውም፤ አሊያም ሕይወታቸውን የሚያሳልፉት ዘላቂ ጥቅም የሌላቸውን ግቦች በማሳደድ ነው። (መዝ. 90:10) እኛ ግን የአምላክ ልጆች እንደመሆናችን መጠን ይሖዋ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ግሩም ተስፋ ስለሰጠን በእርግጥ እንደሚወደን ይሰማናል። ይህ ደግሞ እውነተኛ ትርጉምና ዓላማ ያለው ሕይወት እንድንመራ ያስችለናል።
ይሖዋ ለልጆቹ ምክርና ተግሣጽ ይሰጣል
12. ይሖዋ ለቃየንና ለባሮክ የሰጠው ምክርም ሆነ ማስጠንቀቂያ ለእነሱ ያለውን ፍቅርና አሳቢነት የሚያሳየው እንዴት ነው?
12 “ለምን ተናደድክ? ለምንስ አዘንክ? መልካም ወደ ማድረግ ብታዘነብል ኖሮ ሞገስ አታገኝም ነበር? . . . ታዲያ አንተ [ኃጢአትን] ትቆጣጠረው ይሆን?” (ዘፍ. 4:6, 7) ይህ በትክክለኛው ጊዜ የተሰጠ ጠቃሚ ምክር ነበር። ይሖዋ ለቃየን ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው አደገኛ የሆነ አካሄድ እየተከተለ እንደሆነ ስለተገነዘበ ነው። የሚያሳዝነው ግን ቃየን የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሳይቀበል ቀረ፤ ይህም ለከባድ ችግር ዳርጎታል። (ዘፍ. 4:11-13) የኤርምያስ ጸሐፊ የነበረው ባሮክ በተሰላቸና ደስታ በራቀው ጊዜ ይሖዋ የችግሩ መንስኤ ምን እንደሆነ እንዲያስተውል ምክር ሰጥቶታል። ከቃየን በተቃራኒ ባሮክ ይሖዋ የሰጠውን ምክር በመቀበሉ ሕይወቱን ማትረፍ ችሏል።—ኤር. 45:2-5
13. ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹ መከራ እንዲደርስባቸው የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
13 ጳውሎስ፣ “ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻልና፤ እንዲያውም እንደ ልጁ አድርጎ የሚቀበለውን ሁሉ ይቀጣል” ሲል ጽፏል። (ዕብ. 12:6) ይሁንና ተግሣጽ ሁልጊዜ ቅጣትን ብቻ የሚያመለክት አይደለም። በተለያዩ መንገዶች ሊሰጥ ይችላል። በርካታ የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች ከባድ ፈተና እንደደረሰባቸው የሚገልጹ ዘገባዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው እናገኛለን፤ አንዳንዶቹ ፈተናዎች ተግሣጽንና ሥልጠናን ያካተቱ ናቸው። እስቲ ስለ ዮሴፍ፣ ሙሴና ዳዊት ለማሰብ ሞክር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሕይወት ታሪካቸው ሕያው በሆነ መልኩና በዝርዝር ተመዝግቦ ከምናገኛቸው ግለሰቦች መካከል እነሱም ይገኙበታል። በመከራቸው ወቅት ይሖዋ ከጎናቸው እንዴት እንደነበረና እንዴት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጠቀመባቸው ማንበባችን ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ስለሚያደርግላቸው እንክብካቤም ሆነ ስለሚያሳያቸው ፍቅር ይበልጥ እንድንገነዘብ ይረዳናል።—ምሳሌ 3:11, 12ን አንብብ።
14. ይሖዋ ተግሣጽ ሲሰጠን ፍቅሩን ማስተዋል የምንችለው እንዴት ነው?
14 ይሖዋ የሚሰጠን ተግሣጽ የፍቅሩን ሌላ ገጽታም እንድናስተውል ይረዳናል። የተሳሳተ ድርጊት የፈጸመ አንድ ሰው ይሖዋ ሲገሥጸው ለተግሣጹ ምላሽ በመስጠት ንስሐ ከገባ “ይቅርታው ብዙ” የሆነው አምላክ ይቅር ይለዋል። (ኢሳ. 55:7) ይህ ምን ማለት ነው? ዳዊት የይሖዋን ይቅር ባይነት እንዲህ በማለት ስሜት በሚነካ መንገድ ገልጾታል፦ “እሱ በደልሽን ሁሉ ይቅር ይላል፤ ሕመምሽንም ሁሉ ይፈውሳል፤ ሕይወትሽን ከጉድጓድ ያወጣል፤ ታማኝ ፍቅሩንና ምሕረቱን ያጎናጽፍሻል። ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣ በደላችንን ከእኛ አራቀ።” (መዝ. 103:3, 4, 12) ይሖዋ የሚሰጠን ምክር አልፎ ተርፎም ተግሣጽ ለእኛ ያለውን ታላቅ ፍቅሩን የሚያንጸባርቅ እንደሆነ በመገንዘብ አፋጣኝ ምላሽ እንስጥ።—መዝ. 30:5
ይሖዋ ይጠብቀናል እንዲሁም ይታደገናል
15. ይሖዋ ለሕዝቡ እንደሚሳሳ በምን ማወቅ እንችላለን?
15 አንድ አፍቃሪ አባት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች አንዱ ቤተሰቡን ከጉዳት ወይም አደጋ ሊያደርስ ከሚችል ነገር መጠበቅ ወይም መታደግ እንደሆነ ግልጽ ነው። በሰማይ የሚኖረው አባታችን ይሖዋ ከዚህ ያነሰ ነገር እንደማያደርግ የታወቀ ነው። መዝሙራዊው ስለ ይሖዋ “እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት ይጠብቃል፤ ከክፉዎች እጅ ይታደጋቸዋል” ብሏል። (መዝ. 97:10) አንድ ምሳሌ እንመልከት። መቼም ለዓይንህ በጣም እንደምትሳሳ ግልጽ ነው! ይሖዋ ለሕዝቡ ያለው ስሜትም ልክ እንደዚህ ነው። (ዘካርያስ 2:8ን አንብብ።) በእርግጥም አምላክ ለሕዝቡ በጣም ይሳሳል!
16, 17. ይሖዋ ጥንትም ሆነ ዛሬ ሕዝቡን ከአደጋ እንደሚጠብቅ ያሳየው እንዴት እንደሆነ አብራራ።
16 ይሖዋ ሕዝቡን የሚጠብቅበት አንዱ መንገድ በመላእክቱ አማካኝነት ነው። (መዝ. 91:11) አንድ መልእክ 185,000 ወታደሮችን በአንድ ሌሊት በመደምሰስ ኢየሩሳሌምን ከአሦራውያን ወረራ ታድጓል። (2 ነገ. 19:35) ሐዋርያው ጴጥሮስና ጳውሎስ እንዲሁም ሌሎች ክርስቲያኖች በመላእክት እርዳታ ከእስር ቤት ወጥተዋል። (ሥራ 5:18-20፤ 12:6-11) በእኛም ዘመን ቢሆን የይሖዋ እጅ አጭር አይደለም። አንድ የዋናው መሥሪያ ቤት ተወካይ በአፍሪካ የሚገኝ አንድ ቅርንጫፍ ቢሮ ጎብኝቶ የነበረ ሲሆን አገሪቱ በፖለቲካዊና በሃይማኖታዊ ግጭቶች ሳቢያ ለከፍተኛ ውድመት እንደተዳረገች ሪፖርት አድርጓል። በአገሪቱ ይካሄድ የነበረው ውጊያ፣ ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈርና ግድያ በአገሪቱ ውስጥ ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግሥ አድርጎ ነበር። ምንም እንኳ አብዛኞቹ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ንብረታቸውንና መተዳደሪያቸውን ሙሉ በሙሉ ቢያጡም ሕይወታቸውን ያጡ ወንድሞችም ሆኑ እህቶች የሉም። “እንዴት ናችሁ?” ተብለው ሲጠየቁ “ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን፣ ሁሉም ነገር ሰላም ነው!” በማለት በፈገግታ መልስ ይሰጡ ነበር። እነዚህ ወንድሞች አምላክ እንደሚወዳቸው ማየት ችለዋል።
17 እርግጥ ነው፣ ይሖዋ እንደ እስጢፋኖስ ያሉ ታማኝ አገልጋዮቹ በጠላቶቻቸው እጅ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የፈቀደበት ጊዜ አለ። ይሁንና አምላክ የሰይጣንን መሠሪ ዘዴዎች መቋቋም እንዲችሉ ወቅታዊ ማስጠንቀቂያዎችን በመስጠት ሕዝቡን በአጠቃላይ ከአደጋ ይጠብቃል። (ኤፌ. 6:10-12) ይሖዋ በቃሉና ድርጅቱ በሚያዘጋጃቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች አማካኝነት ሀብት ስላለው የማታለል ኃይል፣ ብልግናና ዓመፅ ስለተሞላባቸው መዝናኛዎች፣ ተገቢ ስላልሆነ የኢንተርኔት አጠቃቀምና ስለመሳሰሉት ነገሮች እውነቱን መገንዘብ እንድንችል ይረዳናል። ከዚህ በግልጽ መረዳት እንደምንችለው ይሖዋ ልክ እንደ አንድ አፍቃሪ አባት ሕዝቡን ከአደጋ ይጠብቃል።
ታላቅ መብት
18. ይሖዋ ስላሳየህ ፍቅር ምን ይሰማሃል?
18 ይሖዋ ለእኛ ያለውን የላቀ ፍቅር የገለጸባቸውን አንዳንድ መንገዶች ከተመለከትን በኋላ የሙሴን ስሜት መጋራታችን አይቀርም። ሙሴ ይሖዋን በማገልገል ያሳለፈውን ረጅም ዘመን መለስ ብሎ በማሰብ “በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እልል እንድንልና ሐሴት እንድናደርግ፣ በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን አጥግበን” ብሏል። (መዝ. 90:14) ይሖዋ ለእኛ ያለውን ፍቅር መረዳትና ማጣጣም መቻላችን እንዴት ያለ በረከት ነው! ደግሞም ይህ በዛሬው ጊዜ ልናገኘው ከምንችለው ሁሉ እጅግ የላቀ መብት ነው። እንደ ሐዋርያው ዮሐንስ ሁሉ እኛም “አብ ምን ያህል ታላቅ ፍቅር እንዳሳየን ተመልከቱ!” ለማለት እንገፋፋለን።—1 ዮሐ. 3:1