መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥር 2014
ይህ የጥናት እትም ይሖዋ ምንጊዜም ንጉሥ መሆኑን ያረጋግጣል። በተጨማሪም መሲሐዊውን መንግሥትና ያከናወነውን ነገር በተመለከተ ያለንን አድናቆት ይጨምርልናል።
ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል—ምዕራብ አፍሪካ
አንዳንድ አውሮፓውያን ወደ ምዕራብ አፍሪካ እንዲሄዱ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? እዚያስ ምን አጋጠማቸው?
የዘላለሙን ንጉሥ ይሖዋን አምልኩ
ይሖዋ አባትነቱን የገለጸበትንም ሆነ ንጉሣዊ ሥልጣኑን የተጠቀመበትን መንገድ መማርህ ወደ እሱ እንድትቀርብ ይገፋፋሃል።
ለ100 ዓመት የዘለቀ ንጉሣዊ አገዛዝ—የአንተን ሕይወት የሚነካው እንዴት ነው?
ከአምላክ መንግሥት አገዛዝ ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? መሲሐዊው ንጉሥ ተገዢዎቹን ያጠራው፣ ያስተማረውና ያደራጀው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።
በወጣትነት ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምርጫ ማድረግ
ራሳቸውን የወሰኑ ብዙ ወጣት ክርስቲያኖች ሌሎችን በመርዳት አስደሳች ተሞክሮ እያገኙ ነው። በይሖዋ አገልግሎት ይበልጥ አስደሳች በሆነ መንገድ መካፈል የምትችለው እንዴት ነው?
የጭንቀት ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ይሖዋን ማገልገል
በዕድሜ የገፉ ክርስቲያኖች አገልግሎታቸውን ለማስፋት ምን ልዩ አጋጣሚዎች አሏቸው?
“መንግሥትህ ይምጣ”—ግን መቼ?
አምላክ የቀባው ንጉሥ መለኮታዊው ፈቃድ ሙሉ በሙሉ በምድር ላይ እንዲሆን በቅርቡ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደሚወስድ እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?
በልጅነቴ ያደረግኩት ምርጫ
በኦሃዮ፣ ኮለምበስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ይኖር የነበረ አንድ ትንሽ ልጅ የካምቦዲያን ቋንቋ ለመማር የወሰነው ለምንድን ነው? ይህን ምርጫ ማድረጉ ሕይወቱን የለወጠው እንዴት ነው?