በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክን ምን መጠየቅ ትፈልጋለህ?

አምላክን ምን መጠየቅ ትፈልጋለህ?

አምላክን ምን መጠየቅ ትፈልጋለህ?

በምድር ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች ሕይወትን በተመለከተ አሳሳቢ ጥያቄዎች አሏቸው። አንተስ? ብዙዎች ጥያቄዎቻቸውን ለሃይማኖታዊ አስተማሪዎች ቢያቀርቡም የሚያረካ መልስ አላገኙም። ሌሎች ደግሞ እነዚህን ጥያቄዎች በውስጣቸው ይዘው ይብሰለሰላሉ። አንዳንዶች መመሪያ ለማግኘት ጸልየዋል። ግራ ለሚያጋቡህ ጉዳዮች በእርግጥ ከአምላክ መልስ ማግኘት የሚቻል ይመስልሃል? ብዙዎች አምላክን መጠየቅ ከሚፈልጓቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

አምላክ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?

ሰዎች ስለ አምላክ የሚኖራቸው አመለካከት ባደጉበት ኅብረተሰብ፣ በወላጆቻቸው ሃይማኖትና አንዳንድ ጊዜም በራሳቸው ምርጫ ላይ የተመካ ነው። አንዳንድ ሰዎች አምልኮ ለሚያቀርቡለት አካል ስም ይሰጡታል ሌሎች ደግሞ በደፈናው አምላክ ብለው ይጠሩታል። ይህ የሚያመጣው ለውጥ ይኖራል? ስሙንና ማንነቱን የሚገልጽልን እውነተኛ አንድ አምላክ አለ?

መከራ የበዛው ለምንድን ነው?

አንድ ሰው ግድ የለሽ መሆኑ ወይም ሥነ ምግባር የጎደለው ሕይወት መምራቱ ለበሽታ ወይም ለድህነት ሲዳርገው በሁኔታው ያማርር ይሆናል። ሆኖም መከራው የደረሰበት ለምን እንደሆነ ያውቃል።

ይሁን እንጂ ሌሎች በርካታ ሰዎች ያለ ጥፋታቸው ከባድ መከራ ይደርስባቸዋል። አንዳንዶች ሥር የሰደደ የጤና እክል አለባቸው። ሌሎች ደግሞ ለቤተሰባቸው መጠለያና በቂ ምግብ ለማግኘት ሲሉ ሊዘለቁ የማይችሉ ከሚመስሉ ችግሮች ጋር ይታገላሉ። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የወንጀል፣ የጦርነት፣ የዓመፅ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ወይም በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች የሚፈጽሙት ግፍ ሰለባ ይሆናሉ።

ከዚህም የተነሳ ብዙዎች ‘እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ይህን ያህል የተስፋፉት ለምንድን ነው? አምላክ ይህ ሁሉ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው?’ በማለት ይጠይቃሉ።

የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?

አብዛኛውን ጊዜ አንድ ሰው በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው እርካታ ማግኘት ሲሳነውና ባዶነት ሲሰማው ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ ይገደዳል። ይህ ደግሞ የብዙ ሰዎች ስሜት ነው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት አስቀድሞ በአምላክ ተወስኗል የሚል እምነት አላቸው፤ ግን ትክክል ናቸው? አምላክ ለአንተ አንድ ዓይነት የተለየ ዓላማ ካለው ይህን ማወቅ እንደምትፈልግ ምንም አያጠራጥርም።

በዓለም ላይ ካሉት መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መሆኑን በግልጽ የሚናገረው አንድ መጽሐፍ ነው። አምላክ ለመላው የሰው ዘር የሚያስተላልፈው መልእክት በብዙ ቋንቋዎች መዳረስ እንዳለበት ሁሉ ይህ መጽሐፍም እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፈ ከማንኛውም መጽሐፍ በበለጠ በብዙ ቋንቋዎች ይገኛል። ይህ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው አምላክ በዚህ መጽሐፍ አማካኝነት ማንነቱንና ስሙን ገልጾልናል። ስሙን ታውቀዋለህ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ ባሕርያት ምን ይላል? አምላክ ከአንተ ምን እንደሚፈልግ የሚናገረውንስ ታውቃለህ?

[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

COVER: Chad Ehlers/Index Stock Photography

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ተራራ:- Chad Ehlers/Index Stock Photography