የይሖዋን አመለካከት ኮርጁ
የይሖዋን አመለካከት ኮርጁ
ዕለቱ መስከረም 14, 2002 ነበር። በዚህ ደስ የሚል ብራ ቀን ኒው ዮርክ፣ ዩ ኤስ ኤ ውስጥ በፓተርሰን የትምህርት ማዕከልና በአካባቢው በሚገኙ ሌሎች ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች የመሰብሰቢያ ቦታዎች ከዓለም ዙሪያ የመጡ 6, 521 ሰዎች ተሰብስበዋል። እነዚህ ሰዎች የተሰበሰቡት የጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የ113ኛው ክፍል ተማሪዎችን የምረቃ ሥነ ሥርዓት ለመከታተል ነበር። ተማሪዎቹ ከ14 አገሮች የተውጣጡ ሲሆን በተመደቡባቸው 19 አገሮች ውስጥ ሚስዮናውያን ሆነው ለማገልገል የሚያስችላቸውን የአምስት ወር ሥልጠና ተከታትለዋል።
የፕሮግራሙ ሊቀ መንበር የ98 ዓመቱ የዕድሜ ባለ ጸጋና የይሖዋ ምሥክሮች የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ኬሪ ባርበር ነበር። ወንድም ባርበር ብዙ ሺህ ተማሪዎችን በሚስዮናዊነት ስላሠለጠነውና 60 ዓመት ሊሞላው ስለተቃረበው ስለ ጊልያድ ትምህርት ቤት ካወሳ በኋላ እንዲህ አለ:- “ተማሪዎቹ በዚህ ትምህርት ቤት አማካኝነት ተጨማሪ ሥልጠና ማግኘታቸው አስደናቂ ውጤቶችን አስገኝቷል። በምድር ዙሪያ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ቅን ሰዎች ራሳቸውን ለይሖዋ ሊወስኑና እውነተኛውን አምልኮ ተቀብለው ቅዱስ አገልግሎት ሊያቀርቡ የቻሉት ሚስዮናውያን ባደረጉላቸው እርዳታ አማካኝነት ነው።”
አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ጊልያድ ከመምጣታቸው በፊት አገልግሎታቸውን የማስፋት ፍላጎት እንዳላቸው በተግባር አሳይተዋል። በካናዳ የሚኖሩ አንድ ባልና ሚስት በአካባቢያቸው ለሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ቻይናውያን ምሥራቹን ለማድረስ ሲሉ ከአንድ ዓመት በላይ ቻይንኛ ተምረዋል። ሌላ ባልና ሚስት ደግሞ በራሳቸው ጥረት የአልባንያ ቋንቋ ከተማሩ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ የመማር ፍላጎት ያላቸውን ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄድ ሰዎች ለመርዳት አልባንያ ውስጥ ኑሮአቸውን መሥርተዋል። ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ ወደ ጊልያድ ትምህርት ቤት ከመጠራታቸው በፊት የአምላክ ቃል አስተማሪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች ተዛውረው በሃንጋሪ፣ በጓቲማላና በዶሚኒካን ሪፑብሊክ ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው።
ተመራቂዎቹ በአፍሪካ፣ በምሥራቅ አውሮፓ፣ በማዕከላዊና በደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በሩቅ ምሥራቅ ወደሚገኘው ምድብ ቦታቸው ከመሄዳቸው በፊት በተመደቡበት ቦታ በሚያከናውኑት ሥራ ሁሉ የአምላክን አመለካከት ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል።
ማንኛውንም ጉዳይ በይሖዋ ዓይን ተመልከቱ
ወንድም ባርበር የመክፈቻውን ንግግር ካቀረበ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ አባል የሆነው ማክስዌል ሎይድ የሚያቀርበውን ንግግር አስተዋወቀ። ወንድም ሎይድ ለንግግሩ የመረጠው ጭብጥ “ማንኛውንም ጉዳይ በአምላክ ዓይን ተመልከቱ” የሚል ሲሆን በንግግሩ ውስጥ ዳዊትንና የአምላክን ልጅ ኢየሱስን በምሳሌነት ጠቅሷል። (1 ሳሙኤል 24:6፤ 26:11፤ ሉቃስ 22:42) ተናጋሪው፣ ተማሪዎቹ በጊልያድ ትምህርት ቤት ያገኙት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ የአምስት ወር ሥልጠና ነገሮችን በአምላክ ዓይን የመመልከት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እንደረዳቸው ከጠቀሰ በኋላ “አዲስ በተመደባችሁበት ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ በምታስጠኑበት ጊዜ ሰዎቹ ማንኛውንም ጉዳይ በአምላክ ዓይን መመልከት እንዲችሉ ለመርዳት ጥረት ታደርጋላችሁ?” የሚል ጥያቄ አነሳ። ተማሪዎቹ ለሌሎች ምክር በሚሰጡበት ጊዜ ማድረግ ያለባቸውንም ሲጠቅስ እንዲህ ብሏል:- “‘በእኔ አመለካከት . . .’ ወይም ‘እኔ እንደሚመስለኝ . . .’ አትበሉ፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ ስለ ጉዳዩ ያለውን አመለካከት እንዲገነዘቡ እርዷቸው። እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ በተመደባችሁበት ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ ለምታስተምሯቸው ሰዎች በረከት ትሆናላችሁ።”
ቀጣዩን ንግግር ያቀረበው የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ጌሪት ሎሽ ነበር። የንግግሩ ጭብጥ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ” የሚል ሲሆን ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን በተለያዩ ጊዜያት “እኔ ከአንተ ጋር ነኝ” በማለት አበረታቷቸው እንደነበረ ጠቀሰ። (ዘፍጥረት 26:23, 24፤ 28:15፤ ኢያሱ 1:5፤ ኤርምያስ 1:7, 8) በዘመናችን እኛም ታማኝነታችንን ጠብቀን እስከኖርን ድረስ በይሖዋ ላይ ተመሳሳይ ትምክህት ማሳደር እንችላለን። ወንድም ሎሽ እንዲህ በማለት አክሎ ተናገረ:- “መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች አገኝ ይሆን ብላችሁ ትጨነቃላችሁ? ከሆነ ይሖዋ ‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝ’ እንዳላችሁ አትዘንጉ። የሚያስፈልገኝን ነገር በማጣት እቸገር ይሆን ብላችሁ ትጨነቃላችሁ? ይሖዋ ‘አልለቅህም ከቶም አልተውህም’ እንዳለ አትርሱ።” (ዕብራውያን 13:5) ወንድም ሎሽ፣ ኢየሱስ ታማኝ ተከታዮቹ ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ሥራ ሲያከናውኑ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ቃል መግባቱን በመጥቀስ ንግግሩን ደመደመ።—ማቴዎስ 28:20
ቀጥሎ የጊልያድ ትምህርት ቤት አስተማሪ የሆነው ሎውረንስ ቦወን “በእሳት የተፈተነ ዋስትና ያለው እምነት ይኑራችሁ” በሚል ጭብጥ ንግግር አቀረበ። ከይሖዋ በስተቀር ሌሎች አማልክትን ማምለክ የማይፈልጉ ሰዎች በሙሉ በኤደን በተነሳው አከራካሪ ጥያቄ ምክንያት የተለያዩ ዕብራውያን 5:8, 9) ይሖዋ ተገቢውን የሙቀት መጠን ተጠቅሞ ወርቅን ከቆሻሻው ከሚለይ አንጥረኛ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። በእሳት ከነጠረ ወርቅ ይልቅ በመከራ የተፈተነ እምነት ዋስትና እንዳለው የታወቀ ነው። ለምን? ወንድም ቦወን “ምክንያቱም በመከራ የተፈተነ እምነት ማንኛውንም ዓይነት ፈተና መቋቋም የሚያስችለን ከመሆኑም በላይ ‘እስከ መጨረሻው’ ለመጽናት የሚያስችል ብርታት ይሰጠናል” ሲል ገለጸ።—ማቴዎስ 24:13
ችግሮች አንዳንዴም ከባድ መከራዎች እንደሚያጋጥማቸው ገለጸ። በይሖዋ ላይ ሙሉ በሙሉ በመተማመንና ፍጹም ታዛዥነቱን እንዲያስመሰክር ሲል ይሖዋ የፈቀዳቸውን ከባድ መከራዎች ችሎ በማሳለፍ ታማኝ ሆኖ የተገኘውን የኢየሱስን ምሳሌ እንዲከተሉ ተመራቂዎቹን አበረታታቸው። (ሌላው የጊልያድ ትምህርት ቤት አስተማሪ ማርክ ኑሜር “እናንተስ ሞገስ ታገኙ ይሆን?” በሚል ጭብጥ ንግግር አቀረበ። ጭብጡ ሳሙኤል “በእግዚአብሔርም በሰውም ፊት ሞገስ” እንዳገኘ በሚናገረው በ1 ሳሙኤል 2:26 ላይ የተመሠረተ ነው። አፍሪካ ውስጥ ከአሥር ለሚበልጡ ዓመታት በሚስዮናዊነት ያገለገለው ወንድም ኑሜር የሳሙኤልን ምሳሌ ከጠቀሰ በኋላ እንዲህ አለ:- “እናንተም አምላክ የሰጣችሁን ሥራ በታማኝነት በማከናወን በአምላክ ፊት ሞገስ ማግኘት ትችላላችሁ። አምላክ ውድ የሆነ የሚስዮናዊነት መብት ሰጥቷችኋል።” ወንድም ኑሜር ተመራቂዎቹ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንደ ቅዱስ አደራ እንዲመለከቱትና ይህን ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የአምላክን አስተሳሰብ እንዲከተሉ አበረታቷቸዋል።
ተማሪዎቹ በትምህርት ላይ በቆዩባቸው ወራት ቅዳሜና እሁድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው ‘የእግዚአብሔር ታላቅ ሥራ’ በአካባቢው ለሚኖሩ ሰዎች ለመናገር የሚያስችል ሰፊ አጋጣሚ አግኝተዋል። (ሥራ 2:11) እንዲያውም ይህን ለማድረግ አሥር የተለያዩ ቋንቋዎችን ተጠቅመዋል። ሌላው የጊልያድ ትምህርት ቤት አስተማሪ ዋላስ ሊቨረንስ “‘የአምላክ ድንቅ ሥራዎች’ ሰዎችን ለሥራ ያንቀሳቅሳሉ” በሚል ጭብጥ ባቀረበው ንግግር ለተወሰኑ ተማሪዎች ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። ወንድም ሊቨረንስ “መንፈስ ቅዱስ በጰንጠቆስጤ ዕለት በሰገነት ላይ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች ስለ ‘አምላክ ድንቅ ሥራ’ እንዲናገሩ ገፋፍቷቸዋል። ዛሬም ይኸው መንፈስ ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ይገፋፋቸዋል” በማለት ተናግሯል። አንዳንዶች ለብዙ ሰዎች ለመመሥከር ካላቸው ፍላጎት የተነሳ አዳዲስ ቋንቋዎችን እስከ መማር ደርሰዋል።
የአምላክን አመለካከት ለመኮረጅ የሚያስችል ተግባራዊ ምክር
በተከታታይ ከቀረቡት ከእነዚህ ንግግሮች በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ አባላት የሆኑት ጋሪ ብሮ እና ዊልያም ያንግ ሚስዮናውያን ተመድበው በሚያገለግሉባቸው የተለያዩ አገሮች ውስጥ የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባላት ሆነው ለሚያገለግሉ ወንድሞችና ለ41 ዓመታት በሚስዮናዊነት ላገለገሉ አንድ ባልና ሚስት ቃለ ምልልስ አደረጉላቸው። ከተሰጡት አስተያየቶች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል:- “ባላቸው ነገር ረክተው የሚኖሩ ሚስዮናውያን በተመደቡበት ጸንተው ይኖራሉ። እንደነዚህ ያሉ ሚስዮናውያን ይበልጥ ትኩረት የሚሰጡት ለመጡበት ዓላማ ነው። እዚያ የተመደቡት ምሥራቹን ለመስበክና ሰዎች ይሖዋን እንዲያውቁ ለመርዳት እንደሆነ አይዘነጉትም።”
ሌላው የአስተዳደር አካል አባል ዴቪድ ስፕሌን “ርቃችሁ አትሄዱም!” በሚል ጭብጥ ንግግር በማቅረብ ፕሮግራሙን ደመደመ። አርባ ስድስቱ ተመራቂዎች ወደ ተለያዩ የምድር ክፍሎች ለመሄድ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው እያለ “ርቃችሁ አትሄዱም” ሲል ምን ማለቱ ነው? ወንድም ስፕሌን “በዚህች ምድር ላይ የትም ሂዱ የት ታማኝነታችሁን ጠብቃችሁ እስከኖራችሁ ድረስ ምንጊዜም በአምላክ ቤት ውስጥ ትሆናላችሁ” በማለት ሁኔታውን አስረዳ። አዎን፣ የታመኑ ክርስቲያኖች በሙሉ በአካል የትም ይሁኑ የት ኢየሱስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በተጠመቀ ጊዜ በተቋቋመው በታላቁ የአምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ወይም የአምላክ ቤት ውስጥ ያገለግላሉ። (ዕብራውያን 9:9) በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ ሰዎች ይሖዋ በምድር ላሉት ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ ቅርብ መሆኑን መስማታቸው ምንኛ አጽናንቷቸው ይሆን! ይሖዋ፣ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት እርሱን በትኩረት ይከታተል እንደነበረ ሁሉ እኛም የትም እንኑር የት ለእኛም ሆነ ለምናቀርበው አገልግሎት ትኩረት ይሰጣል። ስለሆነም በአምልኮ ረገድ ከሌሎች ወንድሞቻችንም ሆነ ከይሖዋና ከኢየሱስ የራቅን አይደለንም።
ከዓለም ዙሪያ የተላኩ ሰላምታዎች ከተነበቡ፣ ተማሪዎቹ የት የት እንደተመደቡ ከተገለጸና ተማሪዎቹ በጊልያድ ትምህርት ቤት ላገኙት ሥልጠና የተሰማቸውን አድናቆት የሚገልጽ ደብዳቤ ከተነበበ በኋላ የፕሮግራሙ ሊቀ መንበር አዲሶቹ ሚስዮናውያን መልካም ማድረጋቸውንና ይሖዋን በማገልገል መደሰታቸውን እንዲቀጥሉ በማበረታታት ፕሮግራሙን ደመደመ።—ፊልጵስዩስ 3:1
[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ስለ ተማሪዎቹ የቀረበ አኃዛዊ መረጃ
የተውጣጡባቸው አገሮች ብዛት:- 14
የተመደቡባቸው አገሮች ብዛት:- 19
የተማሪዎቹ ብዛት:- 46
አማካይ ዕድሜ:- 35.0
በእውነት ውስጥ የቆዩባቸው ዓመታት በአማካይ:- 17.2
በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የቆዩባቸው ዓመታት በአማካይ:- 13.7
[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት 113ኛ ክፍል ተመራቂዎች
ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር ለእያንዳንዱ ረድፍ ተራ ቁጥር የተሰጠው ከፊት ወደ ኋላ ሲሆን ስሞቹ የተጻፉት ከግራ ወደ ቀኝ ነው።
(1) ሊኽታርት ኤም፤ ሆሶኢ ኤስ፤ ቤርክቶልድ ኤ፤ ሊም ሲ፤ አኦኪ ጄ (2) ባጊያሽ ጄ፤ ቡኬ ኤስ፤ ቦሲ ኤ፤ ኦልተን ጄ፤ ኤስኮባር አይ፤ ኤስኮባር ኤፍ (3) ስቶኢካ ኤ፤ ስቶኢካ ዲ፤ ፍሪመዝ ኤስ፤ ካርልሰን ኤም፤ ልብሎ አር (4) ቢያንግኪ አር፤ ቢያንግኪ ኤስ፤ ካሚንስኪ ኤል፤ ጆሴፍ ኤል፤ ፓሪስ ኤስ፤ ልብሎ ኤል (5) ፓሪስ ኤም፤ ስኪድሞር ቢ፤ ሆርተን ጄ፤ ሆርተን ኤል፤ ስኪድሞር ጂ (6) ሊም ቢ፤ ኦልተን ጂ፤ ኪዩሪሲ ኢ፤ ላንግልዋ ኤም፤ ስታይኒንገር ኤስ፤ አኦኪ ኤች (7) ላንግልዋ ጄ፤ ስታይኒንገር ኤም፤ ቦሲ ኤፍ፤ ካሚንስኪ ጄ፤ ቡኬ ጄ፤ ሊኽታርት ኢ፤ ሆሶኢ ኬ (8) ባጊያሽ ጄ፤ ኪዩሪሲ ኤም፤ ካርልሰን ኤል፤ ፍሪመዝ ሲ፤ ቤርክቶልድ ደብልዩ፤ ጆሴፍ አር