በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መኖር ምን ዋጋ አለው?

መኖር ምን ዋጋ አለው?

ከዳያና * ጋር የመገናኘት አጋጣሚ ቢኖርህ ብልህ፣ ተግባቢና ተጫዋች ወጣት እንደሆነች ማሰብህ አይቀርም። ከውጭ ስትታይ ደስተኛ ብትመስልም በውስጧ ያለው የዋጋ ቢስነት ስሜት ግን ለቀናት፣ ለሳምንታት አንዳንድ ጊዜም ለወራት ያሠቃያታል። “ስለ መሞት ያላሰብኩበት አንድም ቀን የለም። እኔ ብሞት ዓለማችን እፎይ እንደምትል ይሰማኛል” ብላለች።

“አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አንድ ሰው ራሱን ሲያጠፋ በዚያው ቅጽበት 200 ሰዎች ራስን የማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ፤ አራት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ራስን ስለ ማጥፋት ያስባሉ።”ዘ ጋዜት፣ ሞንትሪያል፣ ካናዳ

ዳያና ፈጽሞ ራሷን እንደማታጠፋ ተናግራለች። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ፣ መኖሯ ምንም ጥቅም እንደሌለው ይሰማታል። “በጣም የምመኘው ነገር ቢኖር በአደጋ መሞት ነው። ሞትን እንደ ጠላት ሳይሆን እንደ ወዳጅ አድርጌ ማየት ጀምሬያለሁ” ብላለች።

ብዙ ሰዎች እንደ ዳያና የሚሰማቸው ሲሆን እንዲያውም አንዳንዶቹ ራሳቸውን ለማጥፋት አስበው አሊያም ሞክረው ያውቃሉ። ይሁን እንጂ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ራሳቸውን ለማጥፋት ከሚሞክሩ ሰዎች አብዛኞቹ ይህን እርምጃ የሚወስዱት ሕይወታቸውን የማጥፋት ፍላጎት ኖሯቸው ሳይሆን የሚደርስባቸውን መከራ ማጥፋት ስለሚፈልጉ ነው። በአጭሩ እነዚህ ሰዎች ለመሞት ምክንያት እንዳላቸው ይሰማቸዋል፤ በመሆኑም የሚያስፈልጋቸው በሕይወት ለመቀጠል የሚያበቃ ምክንያት ነው።

ታዲያ መኖር ምን ዋጋ አለው? ዋጋ እንዳለው የሚያሳዩ ሦስት ምክንያቶችን እስቲ እንመልከት።

^ አን.3 ስሟ ተቀይሯል።