በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ለጥያቄዎቻችን መልስ ይዟል’

‘ለጥያቄዎቻችን መልስ ይዟል’

‘ለጥያቄዎቻችን መልስ ይዟል’

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች ጥራዝ 2 (እንግሊዝኛ) የተባለውን አዲስ መጽሐፍ በሚመለከት ብዙ ወጣቶች ‘ለጥያቄዎቻችን መልስ ይዟል’ በማለት አስተያየት እየሰጡ ነው። በቴክሳስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖረው ጄሲካ እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “ስለ ራሴ ሁኔታ ግራ ተጋብቼ ነበር። ይህ መጽሐፍ በጣም አበረታቶኛል። አምላክን ለማገልገል ጥረት ሲያደርጉ ልክ እንደ እኔ እንቅፋት የሚያጋጥማቸው በርካታ ወጣቶች እንዳሉ ማወቄ ጠቅሞኛል። መጽሐፉ ወጣትነትን በሚመለከት ለማነሳቸው ጥያቄዎች ሁሉ ለማለት ይቻላል መልስ ይዟል።”

በኮሎራዶ የምትኖረው ብሬን ደግሞ እንዲህ ብላለች፦ “ያዘጋጃችሁት መጽሐፍ በወላጆችና በልጆች መካከል የሐሳብ ልውውጥ እንዲኖር ያበረታታል። እናቴን ላነጋግራት ስፈልግ መጽሐፉን አመጣና በቀጥታ አነብላታለሁ። አንዲት ጓደኛዬም ይህን መጽሐፍ ካነበበች በኋላ አንድን ጉዳይ በሚመለከት ወላጆቿን ለማነጋገር አስባለች።”

የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ አንድን ርዕሰ ጉዳይ ማለትም ከተቃራኒ ጾታ ጋር ጓደኝነት መመሥረትን በሚመለከት በተለይ በወጣቶች አእምሮ ውስጥ ለሚጉላሉ ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣል። በኒው ጀርሲ የምትኖረው ካትሪን እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “አሁን የወንድ ጓደኛ ለመያዝ ጊዜዬ አይደለም፤ ይህ መጽሐፍ ደግሞ ማንም ሰው ምንም ቢለኝ በዚህ ውሳኔዬ ለመጽናት ያደረኩትን ቁርጥ ውሳኔ አጠናክሮልኛል። ከዚህም በላይ አንድ ሰው አለማግባቱ በርካታ ግሩም ነገሮችን ለማድረግ የሚያስችል አጋጣሚ ይከፍትለታል። በአሁኑ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ማከናወኔን ማቆም አልፈልግም። እንዲሁም ጓደኛ ለመያዝ ስደርስ የትዳር ጓደኛዬ እንዲሆን ስለምፈልገው ሰው ምን ማወቅ እንደሚገባኝና ጓደኝነቱን እንዴት መቀጠል እንደምችል የተሻለ ግንዛቤ ይኖረኛል።”

ይህ መጽሐፍ እንዲላክልዎት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ጄሲካ

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ብሬን

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ካትሪን