በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

በመጀመሪያ ራእይ 12:3ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ፤ እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን የጎደሉትን ነገሮች ቦታ ቦታቸው ላይ ሳል።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

ለውይይት:-

ይህ ዘንዶ የሚያመለክተው ማንን ነው? ይህ ዘንዶ በምድር ዙሪያ ባሉት ሕዝቦች ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

ፍንጭ:- ራእይ 12:9ን አንብብ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 3 አምላክ በሰው አእምሮና ልብ ውስጥ ያኖረው ምንድን ነው? መክብብ 3:________

ገጽ 5 የአምላክ ስጦታ ምንድን ነው? ሮሜ 6:________

ገጽ 21 ኢየሱስ በየትኛው ሃይማኖታዊ የማዕረግ ስም መጠቀም እንደሌለብን ተናግሯል? ማቴዎስ 23:________

ገጽ 27 አስተዋይ ሰው ምን ያደርጋል? ምሳሌ 22:________

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

በኢየሱስ የዘር ሐረግ ውስጥ የሚመደበው ማን ነው?

መልሱን ለማግኘት የሚያስችሉህን የሚከተሉትን ፍንጮች ልብ በል። ጥቅሶቹን አውጥተህ አንብብ፤ ከዚያም በተዘጋጀው ክፍት ቦታ ላይ ትክክለኛውን ስም ጻፍ።

4. ․․․․․

ፍንጭ:- ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሠራዊት ይዞ ጥቃት ቢሰነዝርብኝም ይሖዋ ግን በፊቴ ድል አድርጎታል።

2 ዜና መዋዕል 14:9-12ን አንብብ።

5. ․․․․․

ፍንጭ:- በይሁዳ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የይሖዋን ሕግ እንዲማሩ አድርጌያለሁ።

2 ዜና መዋዕል 17:1, 7-9ን አንብብ።

6. ․․․․․

ፍንጭ:- የተቀበርኩት በዳዊት ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አይደለም።

2 ዜና መዋዕል 21:16-20ን አንብብ።

▪ መልሶቹ በገጽ 13 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. አንድ ራስ።

2. አሥር ቀንዶች።

3. ሰባት አክሊል።

4. አሳ።—ማቴዎስ 1:7 NW

5. ኢዮሣፍጥ።—ማቴዎስ 1:8

6. ኢዮራም።—ማቴዎስ 1:8