መልስህ ምንድን ነው?
መልስህ ምንድን ነው?
ይህን የተናገረው ማን ነው?
ዓረፍተ ነገሩንና የተናገረውን ሰው በመስመር አገናኝ።
ሙሴ
ጴጥሮስ
ዮሐንስ
አዳም
1. “ልጆች ሆይ፤ ራሳችሁን ከጣዖቶች ጠብቁ።”
2. ‘ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት።’
3. “ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።”
4. “አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።”
▪ ለውይይት:- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሱት ስለ እነዚህ ሰዎች የምታውቀው ምን ተጨማሪ ሐቅ አለ?
ዘመኑ መቼ ነበር?
ከታች የተዘረዘሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የጻፉትን ሰዎች ስም ጻፍ። ከዚያም መጽሐፉን ተጽፎ እንዳለቀ ከሚገመትበት ዘመን ጋር በመስመር አገናኝ።
1450 ከክ.ል.በፊት 844 ከክ.ል.በፊት 536 ከክ.ል.በፊት 56 ከክ.ል.በኋላ 61 ከክ.ል.በኋላ
5. ዳንኤል
6. ዮናስ
7. ዕብራውያን
እኔ ማን ነኝ?
8. የተመለከትኩት አንድ ተአምር ጉልበቶቼን አብረክርኳቸዋል።
እኔ ማን ነኝ?
9. ከጌታዬ ኮብልዬ የነበረ ቢሆንም ክርስቲያን ስሆን ወደ እሱ ተመልሻለሁ።
ከዚህ እትም
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።
ገጽ 5 ተላላ ወይም ተሞክሮ የጎደለው ማንኛውም ሰው ምን ያደርጋል? (ምሳሌ 14:․․․)
ገጽ 11 ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረው ባሕርይ የትኛው ነው? (ቈላስይስ 3:․․․)
ገጽ 19 ሁላችንም ብዙውን ጊዜ ምን ያጋጥመናል? (ያዕቆብ 3:․․․)
ገጽ 28 ሞት ለሰው ሁሉ የተዳረሰው እንዴት ነው? (ሮሜ 5:․․․)
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
(መልሱ በገጽ 14 ላይ ይገኛል)
በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. ዮሐንስ።—1 ዮሐንስ 5:21
2. አዳም።—ዘፍጥረት 2: 23
3. ጴጥሮስ።—1 ጴጥሮስ 5:8
4. ሙሴ።—መዝሙር 90:2
5. ዳንኤል፣ 536 ከክ.ል.በፊት
6. ዮናስ፣ 844 ከክ.ል.በፊት
7. ጳውሎስ፣ 61 ከክ.ል.በኋላ
9. አናሲሞስ።—ፊልሞና 10-16