ትዳራቸው ከመፍረስ ዳነ
ትዳራቸው ከመፍረስ ዳነ
በደቡብ አፍሪካ የምትኖር አንዲት አሠሪ ቤላ የተባለች ሠራተኛዋ በትዳሯ ውስጥ ችግር እንደገጠማት አስተዋለች፤ በዚህ ጊዜ ታንዲ የምትባለው የይሖዋ ምሥክር ይህቺን ሴት እንድታነጋግራት ጠየቀቻት። ታንዲ ቤላን ቀርባ ስታነጋግራት ባለቤቷን ለመፍታት እንደወሰነች አጫወተቻት።
ታንዲ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ሁለት ቅጂ ለቤላ ካበረከተችላት በኋላ አንዱን ቅጂ ለባለቤቷ እንድትሰጠው አበረታታቻት። ቤላም እንደተነገራት ለባለቤቷ አንዱን መጽሐፍ ሰጠችው። ከሳምንት በኋላ ታንዲ ቤላን ስለ ሁኔታው ስትጠይቃት ባለቤቷ መጽሐፉን እያነበበው መሆኑንና ቤቷም ውስጥ ሰላም መስፈኑን አጫወተቻት። ከሦስት ወር በኋላ ቤላ፣ አምላክ በጸሎትና ለቤተሰብ ደስታ በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ትዳሯን ከመፍረስ እንዳዳነላት ለታንዲ ገለጸችላት። ይሁንና ተሞክሮው በዚህ አያበቃም።
የቤላ አሠሪ የሆነውን ስትሰማ የኩባንያው ሠራተኞች በሙሉ የዚህን መጽሐፍ ቅጂ ቢያገኙ ጥሩ ሊሆን እንደሚችል ሐሳብ አቀረበች። በመጨረሻም የኩባንያው ሠራተኞች ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ከመቶ በላይ ወስደዋል። መጽሐፉ ከያዛቸው ትምህርት ሰጪ ምዕራፎች መካከል “ትዳር በቋፍ ላይ በሚሆንበት ጊዜ፣” “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ” እና “በቤተሰባችሁ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርጉ” የሚሉት ይገኙበታል።
ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።