በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በንቁ! መጽሔት በሚገባ መጠቀም

በንቁ! መጽሔት በሚገባ መጠቀም

በንቁ! መጽሔት በሚገባ መጠቀም

በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖረውና የይሖዋ ምሥክር የሆነችው የ16 ዓመቷ ቫኔሳ አኖሬክሲያ የተባለውን የተዛባ የአመጋገብ ልማድ በተመለከተ ሪፖርት እንድታዘጋጅ የቤት ሥራ ተሰጣት። “አንዳንድ ምርምር ባደርግም ብዙም መረጃ አላገኘሁም” በማለት ትናገራለች። “ጉዳዩን ለወላጆቼ ሳዋያቸው ጽሑፎቻችንን ተጠቅሜ ምርምር እንዳደርግ አበረታቱኝ።”

ቫኔሳ የይሖዋ ምሥክሮች የሚያዘጋጁዋቸውን ጽሑፎች ተጠቅማ ምርምር በማድረግ ለሪፖርቷ የሚሆን ብዙ መረጃ አገኘች። “ሆኖም ሪፖርት ማጠናቀር ብቻ ሳይሆን በመምህሬና በ20 ተማሪዎች ፊት ንግግር ማቅረብም ነበረብኝ!” ትላለች። ታዲያ ቫኔሳ ይህንን ከባድ ሥራ እንዴት ትወጣው ይሆን?

በሁሉም የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች እንደሚያደርጉት ሁሉ ቫኔሳም በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በመገኘት በተሰበሰቡ ሰዎች ፊት ንግግር ለማቅረብ የሚያስችል ሥልጠና ታገኛለች። ቫኔሳ “በዚህ ትምህርት ቤት አማካኝነት አገልግሎት ወጥቶ ሌሎችን ለማነጋገር የሚያስችል ሥልጠና እናገኛለን” በማለት ትናገራለች። “በተጨማሪም ሰዎች የምንናገረውን ይበልጥ እንዲረዱ ለማድረግ ምን ማስተካከያዎች ማድረግ እንደምንችል ምክር ይሰጠናል።” ቫኔሳ ሪፖርቱን ለማዘጋጀት ያደረገችው ጥረት ምን ውጤት አስገኘ? “ከፍተኛውን ነጥብ አገኘሁ” በማለት ተናግራለች።

ቫኔሳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችንና የሚያገኟቸውን ሌሎች መንፈሳዊ ሥልጠናዎች በሚገባ ከሚጠቀሙ በርካታ ወጣቶች መካከል አንዷ ነች። እነዚህ ወጣቶች በመክብብ 12:1 ላይ የሚገኘውን “በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ” የሚል ምክር ተግባራዊ እያደረጉ በመሆናቸው ሊመሰገኑ ይገባል።