በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ከልስ

ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ከልስ

አጥንተህ ከጨረስክ በኋላ፣ ያጠናኸውን ነገር ማስታወስ ከብዶህ ያውቃል? ሁላችንም አልፎ አልፎ እንዲህ ያለ ሁኔታ ያጋጥመናል። ታዲያ ምን ሊረዳን ይችላል? ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች መከለሳችን ይረዳናል።

በምታጠናበት ወቅት በየመሃሉ ቆም እያልክ ስለ ቁልፍ ነጥቦቹ አስብ። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ደብዳቤውን የሚያነብቡ ሰዎች ይህን እንዲያደርጉ ለመርዳት ሲል “እንግዲህ የምንናገረው ነገር ዋና ነጥብ ይህ ነው” ማለቱን ልብ በል። (ዕብ. 8:1) በዚህ መንገድ፣ አንባቢዎቹ የትምህርቱን ትርጉም እንዲሁም እያንዳንዱ ነጥብ ከዋናው ጭብጥ ጋር የሚያያዝበትን መንገድ እንዲያስተውሉ ረድቷቸዋል።

በጥናት ክፍለ ጊዜህ መጨረሻ ላይ በዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ላይ ለማሰላሰል የተወሰነ ጊዜ ምናልባትም አሥር ደቂቃ ገደማ መመደብ ትችላለህ። ነጥቦቹን ማስታወስ ከከበደህ ንዑስ ርዕሶቹን ወይም ፍሬ ሐሳቦቹን የያዙትን ዓረፍተ ነገሮች መለስ ብለህ ተመልከት፤ በአብዛኛው ፍሬ ሐሳቦቹን የያዙት ዓረፍተ ነገሮች የሚገኙት በእያንዳንዱ አንቀጽ መጀመሪያ ላይ ነው። አዲስ ነገር ከተማርክ ትምህርቱን በራስህ አባባል ለማብራራት ሞክር። ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች መከለስህ ነጥቦቹን ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ትምህርቱ ከሕይወትህ ጋር የሚያያዘው እንዴት እንደሆነ ለማስተዋልም ይረዳሃል።