ከአምላክ ቃል ጋር ተዋወቅ
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን መልእክት ወይም ቃል ይዟል። ሕይወታችንን በተሳካ መንገድ መምራት የምንችለው እንዴት እንደሆነና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል። ከዚህም በተጨማሪ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ይዟል፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማውጣት የሚቻልበት ዘዴ
መጽሐፍ ቅዱስ 66 ትናንሽ መጻሕፍትን የያዘ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት የሚከፈል ሲሆን አንደኛው የዕብራይስጥና የአረማይክ ቅዱሳን መጻሕፍት (“ብሉይ ኪዳን”)፣ ሌላኛው ደግሞ የግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት (“አዲስ ኪዳን”) በመባል ይታወቃል። እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ በምዕራፎችና በቁጥሮች የተከፋፈለ ነው። ጥቅሶች በሚጠቀሱበት ጊዜ ከመጽሐፉ ስም ቀጥሎ የሚገኘው የመጀመሪያው ቁጥር የመጽሐፉን ምዕራፍ የሚያመለክት ሲሆን ቀጥሎ ያለው አኃዝ ደግሞ ሐሳቡ የሚገኝበትን ቁጥር የሚጠቁም ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ዘፍጥረት 1:1 ሲባል ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1 ማለት ነው።