መዝሙር 99:1-9
99 ይሖዋ ነገሠ።+ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ።
እሱ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን ተቀምጧል።+ ምድር ትናወጥ።
2 ይሖዋ በጽዮን ታላቅ ነው፤ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው።+
3 ሕዝቦች ታላቅ ስምህን ያወድሱ፤+ስምህ እጅግ የሚፈራና ቅዱስ ነውና።
4 እሱ ፍትሕን የሚወድ ኃያል ንጉሥ ነው።+
አንተ ቅን የሆነውን ነገር በጽኑ መሥርተሃል።
ፍትሕንና ጽድቅን ለያዕቆብ አስፍነሃል።+
5 ይሖዋ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+ በእግሩ ማሳረፊያ ፊት ስገዱ፤*+እሱ ቅዱስ ነው።+
6 ከካህናቱ መካከል ሙሴና አሮን ይገኙበታል፤+ስሙን ከሚጠሩ መካከልም ሳሙኤል አንዱ ነው።+
እነሱ ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤እሱም ይመልስላቸው ነበር።+
7 በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ያነጋግራቸው ነበር።+
ማሳሰቢያዎቹንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠብቀዋል።+
8 አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ መልስ ሰጠሃቸው።+
ይቅር ባይ አምላክ ሆንክላቸው፤+ሆኖም ለሠሯቸው ኃጢአቶች ቀጣሃቸው።*+
9 አምላካችንን ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+በቅዱስ ተራራውም+ ፊት ስገዱ፤*አምላካችን ይሖዋ ቅዱስ ነውና።+