መዝሙር 65:1-13
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። መዝሙር።
65 አምላክ ሆይ፣ በጽዮን+ ውዳሴ ይቀርብልሃል፤የተሳልነውን ለአንተ እንሰጣለን።+
2 ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው* ወደ አንተ ይመጣል።+
3 የፈጸምኳቸው በደሎች አሸንፈውኛል፤+አንተ ግን መተላለፋችንን ይቅር አልክ።+
4 በቅጥር ግቢዎችህ ይኖር ዘንድየመረጥከውና ያቀረብከው ሰው ደስተኛ ነው።+
እኛም በቤትህ፣ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደስህ+ ውስጥ ባሉ ጥሩ ነገሮች እንረካለን።+
5 የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ፍርሃት* በሚያሳድሩ የጽድቅ ተግባሮች ትመልስልናለህ፤+በምድር ዳርቻዎች ሁሉናከባሕሩ ማዶ ርቀው ላሉት መታመኛቸው ነህ።+
6 አንተ* በኃይልህ ተራሮችን አጽንተህ መሥርተሃል፤ኃይልንም ለብሰሃል።+
7 አንተ* የሚናወጡትን ባሕሮች፣ የሞገዶቻቸውን ድምፅ፣የብሔራትንም ነውጥ ጸጥ ታሰኛለህ።+
8 ርቀው በሚገኙ ስፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች ምልክቶችህን አይተው በታላቅ አድናቆት ይዋጣሉ፤+ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ያሉ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋለህ።
9 ምድርን እጅግ ፍሬያማ* በማድረግናበማበልጸግ ትንከባከባታለህ።+
የአምላክ ጅረት በውኃ የተሞላ ነው፤ለሰዎች እህል ትሰጣለህ፤+ምድርን ያዘጋጀኸው በዚህ መንገድ ነውና።
10 ትልሞቿን በውኃ ታረሰርሳለህ፤ የታረሰውንም መሬት* ትደለድላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳታለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።+
11 ዘመኑ ጥሩነትህን እንደ ዘውድ እንዲጎናጸፍ ታደርጋለህ፤በጎዳናዎችህም ላይ የተትረፈረፉ ነገሮች ይፈስሳሉ።*+
12 የምድረ በዳው የግጦሽ መሬቶች ሁልጊዜ እንደረሰረሱ ናቸው፤*+ኮረብቶቹም ደስታን ተጎናጽፈዋል።+
13 የግጦሽ መሬቶቹ በመንጎች ተሞሉ፤ሸለቆዎቹም* በእህል ተሸፈኑ።+
በድል አድራጊነት እልል ይላሉ፤ አዎ፣ ይዘምራሉ።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ።”
^ ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት።”
^ ቃል በቃል “እሱ።”
^ ቃል በቃል “እሱ።”
^ ቃል በቃል “እንድትጥለቀለቅ።”
^ ወይም “ጉብታዎቿንም።”
^ ቃል በቃል “ስብ ይንጠባጠባል።”
^ ቃል በቃል “ያንጠባጥባሉ።”
^ ወይም “ረባዳማ ሜዳዎቹም።”