መዝሙር 60:1-12
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በማስታወሻ አበባ” የሚዘመር። ሚክታም።* የዳዊት መዝሙር። ለትምህርት። ከአራምናሃራይም እና ከአራምጾባ ሰዎች ጋር በተዋጋ ጊዜ፤ ኢዮዓብም ተመልሶ በጨው ሸለቆ 12,000 ኤዶማውያንን ፈጀ።+
60 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ አድርገኸናል፤ መከላከያዎቻችንን ጥሰህ አልፈሃል።+
ተቆጥተኸናል፤ አሁን ግን መልሰህ ተቀበለን!
2 ምድርን አናወጥካት፤ ሰነጣጠቅካት።
እየፈራረሰች ነውና ስንጥቆቿን ጠግን።
3 ሕዝብህ መከራ እንዲደርስበት አደረግክ።
የወይን ጠጅ እንድንጠጣና እንድንንገዳገድ አደረግከን።+
4 አንተን የሚፈሩ ከቀስት መሸሽና ማምለጥ እንዲችሉምልክት አቁምላቸው።* (ሴላ)
5 የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑበቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠን።+
6 አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦
“ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+የሱኮትንም ሸለቆ* አከፋፍላለሁ።+
7 ጊልያድም ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤+ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+
8 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+
በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+
በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+
9 ወደተከበበችው* ከተማ ማን ይወስደኛል?
እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+
10 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+
11 ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።+
12 አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤+ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ “አቆምክላቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ “በቅዱስ ስፍራው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
^ ቃል በቃል “ለራሴ ምሽግ ነው።”
^ “ወደተመሸገችው” ማለትም ሊሆን ይችላል።