መዝሙር 58:1-11

  • በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ

    • ክፉዎች እንዲቀጡ የቀረበ ጸሎት (6-8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* 58  እናንተ የሰው ልጆች፣ ዝም ብላችሁ እያለ ስለ ጽድቅ ልትናገሩ ትችላላችሁ?+ በቅንነትስ መፍረድ ትችላላችሁ?+  2  ይልቁንም በልባችሁ ክፋት ትጠነስሳላችሁ፤+እጆቻችሁም በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ያስፋፋሉ።+  3  ክፉዎች፣ ከተወለዱበት ጊዜ* ጀምሮ መንገድ ስተዋል፤*ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ ሥርዓት የሌላቸውና ውሸታሞች ናቸው።  4  መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤+ጆሮውን እንደ ደፈነ ጉበና* ደንቆሮ ናቸው።  5  ድግምተኞቹ ምንም ያህል ችሎታ ቢኖራቸውጉበናው ድምፃቸውን አይሰማም።  6  አምላክ ሆይ፣ ጥርሳቸውን ከአፋቸው አርግፍ! ይሖዋ ሆይ፣ የእነዚህን አንበሶች* መንጋጋ ሰባብር!  7  ፈስሶ እንደሚያልቅ ውኃ ይጥፉ። አምላክ ደጋኑን ወጥሮ በቀስቶቹ ይጣላቸው።  8  ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ፀሐይን ፈጽሞ እንደማያይ ከሴት የተወለደ ጭንጋፍ ይሁኑ።  9  በእሳት የተቀጣጠለው እሾህ ድስታችሁን ሳያሞቀው፣አምላክ እርጥቡንም ሆነ የሚነደውን ቅርንጫፍ እንደ አውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደዋል።+ 10  ጻድቅ ሰው በክፉዎች ላይ የተወሰደውን የበቀል እርምጃ በማየቱ ደስ ይለዋል፤+እግሮቹ በእነሱ ደም ይርሳሉ።+ 11  በዚህ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ “በእርግጥ ጻድቁ ብድራት ይቀበላል።+ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ተበላሽተዋል።”
ቃል በቃል “ከማህፀን።”
በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።
ወይም “ደቦል አንበሶች።”