መዝሙር 36:1-12

  • የአምላክ ታማኝ ፍቅር

    • ክፉ ሰው አምላክን አይፈራም (1)

    • አምላክ የሕይወት ምንጭ ነው (9)

    • “በብርሃንህ፣ ብርሃን ማየት እንችላለን” (9)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የይሖዋ አገልጋይ የዳዊት መዝሙር። 36  ኃጢአት፣ ክፉውን ሰው በልቡ ውስጥ ሆኖ ያናግረዋል፤በዓይኖቹ ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።+  2  ስህተቱ ምን እንደሆነ ተረድቶ የሠራውን ነገር እንዳይጠላው፣ለራሱ ባለው አመለካከት ራሱን እጅግ ይሸነግላልና።+  3  ከአፉ የሚወጣው የክፋትና የሽንገላ ቃል ነው፤መልካም ነገር ለማድረግ ማስተዋል የለውም።  4  በአልጋው ላይ ሆኖ እንኳ ክፋትን ያውጠነጥናል። ጥሩ ባልሆነ መንገድ ላይ ይቆማል፤መጥፎ የሆነውን ነገር ገሸሽ አያደርግም።  5  ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ እስከ ሰማያት፣+ታማኝነትህ እስከ ደመናት ይደርሳል።  6  ጽድቅህ ግርማ እንደተላበሱ ተራሮች* ነው፤+ፍርዶችህ እንደ ጥልቅ ባሕር ናቸው።+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰውንና እንስሳን ትጠብቃለህ።*+  7  አምላክ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!+ የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ሥር ይሸሸጋሉ።+  8  በቤትህ ውስጥ ተትረፍርፎ የሚገኘውን ነገር* እስኪረኩ ድረስ ይጠጣሉ፤+መልካም ነገሮች ከሚፈስሱበት ወንዝህ ታጠጣቸዋለህ።+  9  የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነው፤+በብርሃንህ፣ ብርሃን ማየት እንችላለን።+ 10  ለሚያውቁህ ታማኝ ፍቅርህን፣ቀና ልብ ላላቸው ደግሞ ጽድቅህን ዘወትር አሳያቸው።+ 11  የትዕቢተኛ እግር እንዲረግጠኝ፣ወይም የክፉዎች እጅ እንዲያፈናቅለኝ አትፍቀድ። 12  ክፉ አድራጊዎች የት እንደወደቁ ተመልከት፤ተመተው ወድቀዋል፤ መነሳትም አይችሉም።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሰውንና እንስሳን ታድናለህ።”
ቃል በቃል “እንደ አምላክ ተራሮች።”
ቃል በቃል “ስቡን።”