መዝሙር 21:1-13
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
21 ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡ በአንተ ብርታት ደስ ይለዋል፤+በማዳን ሥራህ እጅግ ሐሴት ያደርጋል!+
2 የልቡን ፍላጎት አሟልተህለታል፤+የከንፈሩንም ልመና አልከለከልከውም። (ሴላ)
3 የተትረፈረፉ በረከቶች ይዘህ ተቀበልከው፤ምርጥ ከሆነ* ወርቅ የተሠራ አክሊልም በራሱ ላይ ደፋህለት።+
4 ሕይወትን ለመነህ፤አንተም ረጅም ዕድሜ* ብሎም የዘላለም ሕይወት ሰጠኸው።+
5 የማዳን ሥራህ ታላቅ ክብር ያስገኝለታል።+
ሞገስና ግርማ አጎናጸፍከው።
6 ለዘላለም እንዲባረክ አደረግከው፤+ከእሱ ጋር እንዳለህ ሲያውቅ* በጣም ደስ ይለዋል።+
7 ንጉሡ በይሖዋ ይተማመናልና፤+በልዑሉ አምላክ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ፈጽሞ አይናወጥም።*+
8 እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ይይዛቸዋል፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ይይዛቸዋል።
9 በተወሰነው ጊዜ ትኩረትህን በእነሱ ላይ ስታደርግ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ።
ይሖዋ በቁጣው ይውጣቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል።+
10 የሆዳቸውን ፍሬ ከምድር ገጽ፣ዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ።
11 በአንተ ላይ ክፉ ለመሥራት አስበዋልና፤+ሊሳካ የማይችል ሴራ ጠንስሰዋል።+
12 ቀስትህን* በእነሱ ላይ* በማነጣጠርእንዲያፈገፍጉ ታደርጋለህና።+
13 ይሖዋ ሆይ፣ በብርታትህ ተነስ።
ለኃያልነትህ የውዳሴ መዝሙር እንዘምራለን።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ከጠራ።”
^ ቃል በቃል “የቀኖች ርዝማኔ።”
^ ቃል በቃል “በፊትህ ደስታ።”
^ ወይም “ፈጽሞ አይንገዳገድም (አይውተረተርም)።”
^ ቃል በቃል “የደጋንህን አውታር።”
^ ቃል በቃል “በፊታቸው።”