መዝሙር 150:1-6
150 ያህን አወድሱ!*+
አምላክን በተቀደሰ ስፍራው አወድሱት።+
ብርታቱን በሚያሳየው ጠፈር* አወድሱት።+
2 ስለ ብርቱ ሥራዎቹ አወድሱት።+
ወደር የለሽ ስለሆነው ታላቅነቱ አወድሱት።+
3 በቀንደ መለከት+ ድምፅ አወድሱት።
በባለ አውታር መሣሪያና በበገና አወድሱት።+
4 በአታሞና+ በሽብሸባ አወድሱት።
በባለ አውታር መሣሪያና+ በዋሽንት+ አወድሱት።
5 በሚያስተጋባ ሲምባል* አወድሱት።
ኃይለኛ ድምፅ በሚያወጣ ሲምባል+ አወድሱት።
6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያህን ያወድስ።
ያህን አወድሱ!*+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
^ ወይም “ስለ ብርታቱ በሚመሠክረው ሰማይ።”
^ እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል፣ እርስ በርሱ ሲጋጭ ኃይለኛ ድምፅ የሚያወጣን ክብ ቅርጽ ያለው ከብረት የተሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ያመለክታል።
^ ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።