መዝሙር 137:1-9
137 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣+ በዚያ ተቀምጠን ነበር።
ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።+
2 በመካከሏ* በሚገኙ የአኻያ ዛፎች ላይበገናዎቻችንን ሰቀልን።+
3 የማረኩን ሰዎች በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤+የሚያፌዙብን ሰዎች በመዝሙር እንድናዝናናቸው
“ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።
4 የይሖዋን መዝሙርበባዕድ ምድር እንዴት ልንዘምር እንችላለን?
5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺን ብረሳ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።*+
6 ሳላስታውስሽ ብቀር፣ኢየሩሳሌምን ለደስታዬ ምክንያትከሆኑት ነገሮች በላይ ባላደርግ፣+ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ትጣበቅ።
7 ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀንኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤
“አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!”+ ብለው ነበር።
8 በቅርቡ የምትጠፊው አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣+በእኛ ላይ በፈጸምሽው በዚያው ድርጊትብድራትሽን የሚመልስ ደስተኛ ይሆናል።+
9 ልጆችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ+ደስተኛ ይሆናል።