ፍቅር
ይሖዋ ፍቅር ያሳየው እንዴት ነው?
ኤር 31:3፤ ዮሐ 3:16፤ ሮም 5:8፤ 1ዮሐ 4:8, 19
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ዘፍ 1:1, 26-31፤ 2:8, 9, 15, 16—ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ ምድርን ለመኖሪያነት አመቻችቷታል፤ ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች ኤደን ገነትንና የተትረፈረፈ በረከት ሰጥቷቸዋል
መዝ 104:27-30—መዝሙራዊው፣ ይሖዋ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ በፍቅር ስለሚንከባከብ አመስግኖታል
ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ዮሐ 13:34, 35፤ 15:12, 13፤ 1ጴጥ 4:8፤ 1ዮሐ 4:10, 11፤ 5:3
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
ማቴ 22:36-39—ኢየሱስ ከሁሉ የሚበልጡትን ሁለት ትእዛዛት ተናግሯል፤ ሁለቱም ከፍቅር ጋር የተያያዙ ናቸው
1ቆሮ 13:1-8—ሐዋርያው ጳውሎስ ፍቅር አስፈላጊ መሆኑን እንዲሁም ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተናግሯል