እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል

ይህ ብሮሹር በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ሰዎች እምነታቸውን በማጠናከር ደስታ ማግኘት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

መግቢያ

መግቢያ

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሳሳቢ ለሆኑ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ አግኝተዋል።

ክፍል 1

አምላክ ስለ እኛ ያስባል?

ዓለማችን በችግር የተሞላ ነው። አንተም ብትሆን በየቀኑ የሚያስጨንቁ ነገሮች ያጋጥሙህ ይሆናል። ታዲያ ማን ሊረዳን ይችላል? ስለ እኛ የሚያስብ አካል ይኖር ይሆን?

ክፍል 2

እውነተኛ እምነት ምንድን ነው?

አምላክ መኖሩን የሚያምኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ፤ ይሁንና ሆን ብለው ክፉ ድርጊት ይፈጽማሉ። እውነተኛ እምነት ማዳበር አምላክ መኖሩን ከማመን ያለፈ ነገርን ይጨምራል።

ክፍል 3

የሰዎችን ሕይወት የሚያሻሽል ጠቃሚ ምክር

ቅዱሳን መጻሕፍት በትዳር ውስጥ የሚያጋጥምን ችግር ለመፍታት፣ ቁጣን ለመቆጣጠር፣ የዕፅ ሱስን ለማሸነፍ፣ የዘር ጥላቻንና ዓመፀኝነትን ለማስወገድ እንዲሁም ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት የሚረዳ ጥበብ ያዘለ ምክር ይዘዋል።

ክፍል 4

አምላክ ማን ነው?

ሰዎች ብዙ አማልክት ያመልካሉ። ይሁን እንጂ ቅዱሳን መጻሕፍት እውነተኛው አምላክ አንድ ብቻ እንደሆነ ያስተምራሉ።

ክፍል 5

የአምላክን ግሩም ባሕርያት ማወቅ

ቅዱሳን መጻሕፍት የአምላክን በርካታ ድንቅ ባሕርያት ይገልጻሉ፤ ይህም ስለ አምላክ ይበልጥ ለማወቅ ይረዳናል።

ክፍል 6

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

ቅዱሳን መጻሕፍት አምላክ ‘ምድርን መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ እንዳልፈጠራት’ ይናገራሉ። ይሁንና በዛሬው ጊዜ ሁኔታዎች እሱ እንዳሰበው ናቸው?

ክፍል 7

አምላክ በነቢያቱ በኩል የሰጠው ተስፋ

ለምድር ሕዝብ ሁሉ የሚሆን በረከት!

ክፍል 8

መሲሑ መጣ

ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ መሲሑ ሕይወትና ስላስተማራቸው ነገሮች ይነግሩናል።

ክፍል 9

መሪ እንዲሆን ከተሾመው መሲሕ መማር

አምላክ ምን ዓይነት መሪ እንደሚያስፈልገን ስለሚያውቅ ከሁሉ የተሻለውን መሪ መርጦልናል።

ክፍል 10

የእውነተኛው እምነት ጠላት ተጋለጠ

አንድ መልአክ የአምላክ ተቃዋሚ ሆነ።

ክፍል 11

በዛሬው ጊዜ እውነተኛ እምነት ማሳየት

ኢየሱስ፣ እውነተኛ እምነት ያላቸው ሰዎች “መልካም ፍሬ” ወይም መልካም ባሕርያት እንደሚያፈሩ አስተምሯል። ከእነዚህ ባሕርያት አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?

ክፍል 12

እውነተኛ እምነት እንዳለህ አሳይ!

ምን እርምጃ መውሰድ ትችላለህ?

ክፍል 13

እውነተኛ እምነት ለዘላለም ደስታ ያስገኝልሃል

ቅዱሳን መጻሕፍት ወደፊት የምታገኘውን አስደናቂ ተስፋ ይዘዋል።