ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?

ስለ ሕይወት አመጣጥ የምታምነው ነገር ለውጥ ያመጣል።

መግቢያ

ፕላኔታችን ሕይወት እንዲኖርባት ታስባ የተዘጋጀች ናት? የዝግመተ ለውጥ ትምህርት ሙሉ በሙሉ በሐቅ ላይ የተመሠረተ ነው?

አንተ የምታምነው በምንድን ነው?

በአምላክ የምታምን እንዲሁም ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ያለህ ሰው ብትሆንም ሕይወት በፍጥረት እንደተገኘ የማያምኑ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው የሳይንስ ሊቃውንት ለሚሰነዝሩት አስተያየት ትልቅ ግምት ትሰጥ ይሆናል።

ሕይወት ያላት ፕላኔት

አንዳንዶች በአጋጣሚ የተከሰቱ እንደሆኑ የሚያስቧቸው በርካታ ነገሮች ባይኖሩ ኖሮ በምድር ላይ ሕይወት የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም ነበር። እነዚህ ነገሮች የተገኙት በአጋጣሚ ነው ወይስ የማሰብ ችሎታ ያለው ፈጣሪ ስለሠራቸው?

የመጀመሪያውን ንድፍ ያወጣው ማን ነው?

ተመራማሪዎች በምሕንድስና መስክ አስቸጋሪ የሆኑባቸውን ነገሮች ለመፍታት የፍጥረታትን ንድፍ ይኮርጃሉ። ቅጂውን ለመሥራት የማሰብ ችሎታ የሚያስፈልግ ከሆነ የዋናውን ንድፍ ለመሥራትስ?

ዝግመተ ለውጥ—ሐቁን ከመላ ምቶች መለየት

የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ከተመሠረተባቸው እሳቤዎች አንዱ፣ ነባር የሆነ አንድ የዕፅዋት ወይም የእንስሳት ዝርያ በሚውቴሽን አማካኝነት ሙሉ በሙሉ አዲስ ወደሆነ ሌላ ዝርያ ተለውጧል የሚል ነው። ይህ ጽንሰ ሐሳብ በሐቅ ላይ የተመሠረተ ነው?

ሳይንስና የዘፍጥረት ዘገባ

ስለ ፍጥረት የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ስህተት መሆኑን ሳይንስ አረጋግጧል?

የምታምነው ነገር ለውጥ ያመጣል?

ዝግመተ ለውጥን በተመለከተ የምታምነው ነገር ስለ ሕይወት ትርጉም ባለህ አመለካከት ላይ ለውጥ ያመጣል?

ዋቢ ጽሑፎች

ይህ ብሮሹር መሠረት አድርጎ የተጠቀመባቸውን ጽሑፎች ተመልከት።